ጤናን ለመጠበቅም ሆነ የህዝብ ለህዝብ ትስስርን ለማጎልበት ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ትኩረት ሊሰጠዉ እንደሚገባ ተመላከተ
በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ወረዳ ጤናዬን እጠብቃለሁ ምርጫን እመርጣለሁ በሚል መሪ ሃሳብ ህዝባዊ የስፖርት እንቅስቃሴና ዉድድር ተካሂዷል።
በጌዴኦ ዞን የይርጋጨፌ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ዘርሁን አሰፋ በመርሃ ግብሩ ማስጀመሪያ ንግግራቸዉ እንደገለጹት፤ ስፖርት በርካታ ዜጎችን በአንድነት የሚያሰባስብ የፍቅር መድረክ በመሆኑ በተለይ ወጣቱ ትዉልድ የራሱን ጤና በመጠበቅ የሃገርን ሠላም ለማጽናት ብርቱ ትግል ማድረግ ይጠበቃል።
የወረዳዉ ህዝብ በስፖርት ሜዳው ያሳየዉን አንድነት ሠላማዊ ምርጫን በማካሄዱ ሂደትም በንቃት እንዲሳተፍ ኃላፊው አሳስበዋል።
የወረዳዉ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግዛቸው ጥላሁን፤ በወረዳው በሚገኙ ሁሉም ማዕከላት መሰል መርሃ-ግብሮችን በማካሄድ ጤናን ከመጠበቅ በተጓዳኝ የህዝብ ለህዝብ ትስስርን ለማጎልበት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ አብራርተዋል።
በስፖርታዊ እንቅስቃሴ ከተሳተፉት መካከል አቶ አበራ አሰፋና መልካሙ ታደለ፤ በስፖርቱ በመሳተፋቸው እንዳስደሰታቸው ገልጸዉ በስፖርት ሜዳ ያሳዩትን አንድነት በጠቅላላ ምርጫውም እንደሚደግሙት ተናግረዋል።
ዘጋቢ: አማኑኤል ትዕግስቱ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
ጤናን ለመጠበቅም ሆነ የህዝብ ለህዝብ ትስስርን ለማጎልበት ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ትኩረት ሊሰጠዉ እንደሚገባ ተመላከተ

More Stories
የወባ ቅድመ መከላከል ስራ ውጤት እያስገኘ መምጣቱን በካፋ ዞን ዴቻ ወረዳ የሚገኙ ነዋሪዎች ተናገሩ
በኢትዮጵያ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት የደቡብ ማዕከል ድጋፍ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በጉራፈርዳ ወረዳ ሩዝ ያመረቱ አርሶ አደሮች ምርታማ መሆናቸውን ገለፁ
በክልሉ የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎትን ከ1.3 ሚሊዮን በላይ ለሆኑ እናቶችና ሴቶች ተደራሽ በማድረግ ጤናቸው እንዲጠበቅ በትኩረት መሠራቱን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ገለፀ