ቤን ዋይት ከዓመታት በኋላ ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ጥሪ ቀረበለት
የአርሰናሉ የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች ቤን ዋይት ከዓመታት በኋላ ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ጥሪ ቀርቦለታል።
በያዝነው ሳምንት ከኡራጓይ እና ጃፓን ጋር የአቋም መለኪያ የምታከናውነው እንግሊዝ ከቀናት በፊት ለ35 ተጫዋቾች ጥሪ ማቅረቧ ይታወቃል።
ጥሪ ከቀረበላቸው ተጫዋቾች መካከል የቀድሞ የሊቨርፑል በአሁኑ ወቅት ለባየር ሊቨርኩሰን እየተጫወተ የሚገኘው ጃሬል ኳንሳህ በጉዳት ምክንያት ከስብስቡ ውጪ ሆኗል።
በምትኩም አሰልጣኝ ቶማስ ቱሄል ለ28 ዓመቱ ተጫዋች ቤን ኋይት ጥሪ አቅርበዋል።
ቤን ኋይት ከ2022 የኳታሩ የዓለም ዋንጫ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሦስቱ አናብስት ጥሪ የተደረገለት።
በተጨማሪም እንግሊዝ የአርሰናሉ ኢቤሪቼ ኢዜ ጉዳት ማስተናገዱን ተከትሎ ለኒውካስሉ የፊት መስመር ተጫዋች ሀርቬይ ባርንስ ጥሪ አድርጋለች።
ዘጋቢ፡ሙሉቀን ባሳ

More Stories
ካርሎስ ባሌባ ለማንቼስተር ዩናይትድ ፊርማውን አኖረ
አርሰናል ከ ላምፓርዱ ኮቨንተሪ ሲቲ
አርሰናል ኤዝሪ ኮንሳን በ55 ሚሊዮን ፓውንድ የዝውውር ሂሳብ አስፈረመ