ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች የሚካፈሉባቸው ውድድሮች ዛሬ
ይካሄዳሉ
በትናንትናው ዕለት በፖላንድ ቶሩን ከተማ መካሄድ በጀመረው 21ኛው የአለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚሳተፉባቸው ውድድሮች ዛሬ ይካሄዳሉ።
በወጣው መርሐግብር መሰረት የ800 ሜትር ሴቶች የግማሸ ፍፃሜ ውድድር፤ ከቀኑ 8:20 ጀምሮ ይካሄዳል።
በርቀቱ አትሌት ንግስት ጌታቸው በሶስተኛው ምድብ ወደ ፍፃሜ ለማለፍ ትወዳደራለች።
አትሌት ንግስት በመጀመሪያው ዙር ማጣሪያ ከምድብ አራት 2:02.89 በመግባት በአንደኝነት ማጠናቀቋ ይታወሳል።
ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ ደግሞ የሴቶች 3000 ሜትር የፍፃሜ ውድድር ይከናወናል።
በውድድሩ አትሌት አለሺኝ ባወቀ እና ፍሬወይኒ ኃይሉ ኢትዮጵያን ይወክላሉ።
እንዲሁም የወንዶች 3000 ሜትር የፍፃሜ ውድድር ምሽት 3:22 ጀምሮ ይከናወናል።
አትሌት አዲሱ ይሁኔ እና ጌትነት ዋለ በኢትዮጵያ በኩል ተወዳዳሪ አትሌቶች ናቸው።
ዘጋቢ፡ሙሉቀን ባሳ

More Stories
“አስተናጋጃችን ፊፋ ነው እንጂ ትራምፕ አይደሉም!” – ኢራን
አርሰናል የእንግሊዝ ባለጸጋ ለመሆን ተቃርቧል!
ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን እንዲያረጋግጡ ምቹ ሁኔታ ከመፍጠሩ ባሻገር በውሳኔ ሰጪነት ቦታዎች ላይ ኃላፊነት በመስጠት ሀገራዊ ራዕይ እያሳካ እንደሚገኝ በኣሪ ዞን የሚገኙ የብልጽግና ፓርቲ የሴቶች ክንፍ አባላት ገለፁ