በዳውሮ ዞን ገና ወረዳ የብልፅግና ፓርቲ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የምረጡኝ ቅስቀሳና የፓርቲ ምርጫ ምልክት የማስተዋወቅ መርሃ ግብር ተካሄደ
በቦታው ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የክልሉ ንግድ፣ ኢንዱስትሪና ገበያ ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ ታሪኩ አካሉ፤ በለውጡ ዓመታት የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች መከናወናቸውን በመጠቆም ፓርቲው ዜጎችን በሁሉም ዘርፎች የሚያሳትፍ አካታችና አሳታፊ ነው ሲሉም ገልጸዋል።
አክለውም ምርጫ ለአንድ አገር ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ መሠረት መሆኑን በመጠቆም ህዝቡ ዲሞክራሲያዊ መብቱን ተጠቀሞ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታን ለማጠናከርና ልማትን ለማፋጠን ያስችላል የሚለውን ፓርቲ መምረጥ እንዳለበት ተናግረዋል፡፡
የመደመር መንግሥት የኢትዮጵያን ብልጽግና እውን ማድረግ የሚያስችል አስተማማኝ መሠረት መጣሉን አስገንዝበዋል።
የዳውሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየሁ፤ ፓርቲው በጌና ወረዳና በአካባቢው እያከናወናቸው ያሉ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች የህዝቡን ህይወት በመቀየር ላይ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
እነዚህን የልማት ሥራዎች አጠናክሮ ለማስቀጠልና የሕዝቡን ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ ኅብረተሰቡ ከፓርቲው ጎን በመቆም የተጀመረውን የለውጥ ጉዞ እንዲያፋጥን ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በቅስቀሳና ድጋፍ ሰልፉ ላይ የተገኙት የወረዳው ነዋሪዎች እንደገለፁት፤ በብልጽግና ፓርቲ መሪነት ባለፉት የለውጥ ዓመታት በሀገሪቱ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ስራዎች ተከናውነዋል፡፡
በተለይም ለሰው ተኮር ፕሮጀክቶች በተሰጠው ትኩረት በሌማት ትሩፋት፣ ለአቅመ ደካሞች ቤቶች ግንባታና በሌሎች ታላላቅ ፕሮጀክቶች ህብረተሰቡ ተጠቃሚ እየሆነ ነው ብለዋል።
በምረጡኝ ቅስቀሳው ብልጽግና ፓርቲን በየደረጃው የሚወክሉ እጩዎች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፡ አሸናፈ ግዛው – ከዋካ ጣቢያችን

More Stories
የባስኬቶ ዞን ላስካ ዙሪያ ወረዳ ህዝብ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 10ኛ አመት የሥራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ጉባኤውን አካሂዷል
የሕዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ምክር ቤቶች ዘርፈ ብዙ ተግባራትን ማከናወን እንደሚገባቸው የኮንሶ ዞን ህዝብ ምክር ቤት ገለጸ
የተፈጥሮ ሀብትን ለመጠበቅ አሳታፊ እና የተቀናጀ የመሬት አጠቃቀም ዕቅድ ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ