1ሺህ 447ኛ የኢድ አል ፈጥር በዓል በኮሬ ዞን ኬሌ ከተማ አሰተዳደር በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ተከበረ
በዓሉ በተክቢራ፣ በኢድ-ሶላትና በሌሎች መንፈሳዊ ሥነ-ሥርዓት በርካታ ህዝበ ሙስሊም በተገኙበት በአደባባይ በድምቀት ተከብሯል።
በበዓሉ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የኮሬ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታረቀኝ በቀለ፥ የረመዳንን ጾም በእዘነት፣ በመረዳዳትና በሠላም መጠናቀቅ በመቻሉ መላው በዞኑ የሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ደስ አላችሁ ሲሉ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
ሙስሊሙ ማህበረሰብ በረመዳን ወር ሲያከናውን የነበረውን የመረዳዳት እሴትና መልካም ተግባራትን በዓሉ በሚከበርበት ወቅትም ማሰቀጠል እንደሚገባ አሳስበዋል።
የኬሌ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ኢንጂነር ዮሐንስ ሐይሉ በበኩላቸው፥ አንድ መሪ ራሱን ካልገዛ ህዝብን ሊመራ እንደማይችል ገልፀው የረመዳን ጾምም ለስጋችን የሚጠቅመንን ነገር ትተን የመንፈስን ነገር የምናስበልጥበት በመሆኑ ራስን መግዛትን ያስተምረናል ብለዋል።
አክለውም በዚህ በአንድ ወር ውስጥ የተማርነው ትዕግስት ለከተማችን እና ለቤተእምነቱ ግንባታ የሚጠቅም መሆኑን ተናግረዋል።
የኢድ አልፈጥር በዓልን ሲያከብሩ ካገኘናቸው መካከል አብዱርከድር ሙስጠፋ፣ ሀሚዲያ አብዱረሽድና ሌሎችም ዛሬ ጁማኣ መሆኑ የዘንድሮውን ኢድ ልዩ እንደሚያደርገዉ ገልጸዉ እንደዚህ በደመቀ ሁኔታ በዓሉን በማክበራቸዉ ደስተኞች መሆናቸዉን ተናግረዋል።
ዘጋቢ: ባዩሽ ኢሳያስ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
1ሺህ 447ኛ የኢድ አል ፈጥር በዓል በኮሬ ዞን ኬሌ ከተማ አሰተዳደር በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ተከበረ

More Stories
መሬት ውስን የተፈጥሮ ሀብት በመሆኑ በአግባቡ በመምራትና ከብክነት በመጠበቅ ቀጣይነት ያለዉን ልማት ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለፀ
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ
መስቀል የድህነት ምልክት መሆኑን የካፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮና ምዕራብ ኦሞ አህጉረ-ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ህዝቅኤል ተናገሩ