የሳውላ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም ወንጀልን የሚጸየፉ አምራች ዜጎችን ለማፍራት በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገለፀ
የሳውላ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም አዛዥ ኢንስፔክተር ታረቀኝ አጥናፉ፤ ተቋሙ ከማረምና ማነጽ ጎን ለጎን ታራሚዎች የሙያ ባለቤት እንዲሆኑና ራሳቸዉን በኢኮኖሚ እንዲያሳድጉ ምቹ ሁኔታ እየፈጠረ ነው ብለዋል።
በኢንተርፕራይዝ በማደራጀት ከሳውላ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ጋር በመቀናጀት ለታራሚዎች ስልጠና በመስጠት ከራሳቸው አልፈው ቤተሰባቸውን እየደገፉ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በማረሚያ ተቋሙ ሰብዓዊ መብታቸዉ ተከብሮ አምራች፣ ብቁ ዜጋ ሆነዉና ታንፀዉ ማህበረሰቡን እንዲቀላቀሉ በተቋሙ አሰፈላጊው የሙያና ክህሎት ስልጠናዎች እየተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ማረሚያ ተቋሙ በስነ-ምግባር የታነጹ ታራሚዎችን ለመፍጠር በርካታ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝና በማረምና ማነጽ ዙሪያ ለታራሚዎች በየጊዜው የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት እየተሰጠ መሆኑን ገልጸዋል።
ሴት ታራሚዎች ድጋፍ በሚያስፈልጋቸዉ ጉዳዮች ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ እየሰሩና በርካታ ድጋፍ እየተደረገ እንዳለ ተናግረዋል።
በማረሚያ ተቋም የእርምት ጊዜያቸውን ጨርሰው ወደ ህብረተሰቡ የሚመለሱ ግለሰቦችን ማህበረሰቡ ታርመውና ታንጽው እንደተመለሱ አድርገው መቀበል እንዳለባቸውም መልዕክት አስተላልፈዋል።
አስተያየታቸዉን የሰጡ የህግ ታራሚዎች፤ ወንጀል አስከፊ በመሆኑ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሕይወታቸው ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማስከተሉን ተናግረዋል።
ወደ ህብረተሰቡ ሲቀላቀሉ ከወንጀል የነጻና መልካም ስነ-ምግባር የተላበሰ ዜጋ ለመሆን ማቀዳቸውን ገልጸዋል።
ዘጋቢ፡ ስንታየሁ ሙላቱ – ከሳውላ ጣቢያችን

More Stories
መሬት ውስን የተፈጥሮ ሀብት በመሆኑ በአግባቡ በመምራትና ከብክነት በመጠበቅ ቀጣይነት ያለዉን ልማት ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለፀ
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ
መስቀል የድህነት ምልክት መሆኑን የካፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮና ምዕራብ ኦሞ አህጉረ-ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ህዝቅኤል ተናገሩ