ከተረጂነት በመውጣት የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ የሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም መሸፈን እንደሚገባ ተገለጸ
በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ወረዳ “ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለተሟላ ሀገራዊ ክብር እና ሉአላዊነት” በሚል መሪ ቃል የውይይት እና ከየቀበሌያት የተሰበሰቡ እህል እና ቁሳቁስ ለወረዳው አስተዳደር ገቢ ተደርገዋል።
ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በሚለው መርህ ትኩረት ተሰጥቶ በመሠራቱ ውጤታማ በመሆን ማህበረሰቡ ራሱን ችሎ ለሰብአዊ ድጋፍ የበኩሉን አስተዋፅኦ እያበረከተ ይገኛል።
በዞን ደረጃ ለመሰብሰብ አቅደን የጀመርነው 72 ሚሊዮን መጠባበቂያ ፈንድ በይርጋጨፌ ወረዳ በእህል እና በቁሳቁስ መልክ የተጀመረው የማሰባሰቡ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል ሲሉ የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ(ዶ/ር) ተናግረዋል።
ይህም በሀገር አቀፍ ደረጃ ለተጀመረው ሥራ እያንዳንዱ አመራር ህብረተሰቡን በማንቀሳቀስና ትኩረት ሰጥቶ በመሥራት ተግባሩ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ማድረግ ይጠበቅበታል ብለዋል።
የይርጋጨፌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ቡኔ፤ በወረዳው ባሉ ሁሉም ቀበሌያት ህብረተሰቡ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት የሚለውን ሀሳብ ተቀብሎ በመሥራት
አሁን ላይ ለሰብዓዊነት ከየቀበሌው እህል በመሰብሰብ በወረዳ ማዕከል የማስረከቡ ሥራ ተሠርቷል ሲሉ ተናግረዋል።
በቀጣይም በሰብአዊነት ራሳችንን ለመቻል የጀመርነውን ሥራ አጠናክረን ከማስቀጠልም ባሻገር በእያንዳንዱ ቀበሌ ያለው ማህበረሰብ ሠርቶ ምርታማ እንዲሆን በማድረግ ከተረጂነት መንፈስ ነፃ እና ራሱን የቻለ ማህበረሰብ መፍጠር ይኖርብናል ሲሉ ተናግረዋል።
ከተሳታፊዎች መካከል አርሶአደር አክሊሉ ወብዩ እና ጴጥሮስ በዳሶ፤ በቀበሌያቸው ከተረጂነት ለመውጣት በሚደረገው ጥረት ህብረተሰቡ የሚጠበቅበትን እህል በማዋጣት በወረዳ ደረጃ እንድናስረክብ ተደርጓል ብለዋል።
በመጪው ጊዜያትም ህብረተሰቡም ሆነ እኛ በግላችን ባለን ማሳ ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር ትኩረት ሰጥተን በመሥራት የሰብአዊ ድጋፉን እናስቀጥላለን ሲሉ አስረድተዋል።
ዘጋቢ፡ አብዶ አያላ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
ከተረጂነት በመውጣት የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ የሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም መሸፈን እንደሚገባ ተገለጸ

More Stories
ውድና ውስን የሆነውን መሬት ያለብክነት ለመምራትና ለመጠቀም እየተሰራ ነው – የባስኬቶ ዞን አስተዳደር
በጎፋ ዞን ጋልማ ከተማ በ2019 በጀት ዓመት ከ18 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል ለመፍጠር መታቀዱ ተገለፀ
የሀድያ ብሔር የዘመን መለወጫ “ያሆዴ” በዓልን ለማክበር በቂ ዝግጅት መደረጉ ተገለጸ