የጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር በምስራቅ ጉራጌ ዞን ምስራቅ መስቃን ወረዳ “ጉዞ ወደ አረንጓዴ ልማት” 14ኛ ዙር የችግኝ ተከላ ፕሮግራም እያካሄደ ይገኛል
ሀዋሳ፡ ሐምሌ 25/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምስራቅ ጉራጌ ዞን በምስራቅ መስቃን ወረዳ ኢሌ ቀበሌ በሙዞ አቤላሞ ተፋሰስ “ጉዞ ወደ አረንጓዴ ልማት” 14ኛ ዙር የችግኝ ተከላ መርሃግብር በመካሄድ ላይ ይገኛል።
የጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር ላለፉት 13 ተከታታይ ዓመታት ባካሄደው የችግኝ ተከላ መርሃግብር ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ በመገንባት ረገድ ዓይነተኛ ሚና መጫወቱም ተገልጿል።
እንደ ሀገር “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሔደ የሚገኘውን የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር መነሻነት ነው ዘንድሮ ለ14ኛ ጊዜ በመካሄድ ላይ የሚገኘው።
ተግባሩ የህዝብ ለህዝብ ተስስርን ከማጠናከር አንፃር ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክትም ተመላክቷል፡፡
በዚህ የጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር ባዘጋጀው የችግኝ ተከላ መርሃግብር ላይ ከፌደራል፣ ከክልል እና ከሁለቱ የጉራጌ ዞኖች የተውጣጡ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በመሳተፍ ላይ ናቸው።
ዘጋቢ፡ መሐመድ ሽሁር – ከወልቂጤ ጣቢያችን

More Stories
ውድና ውስን የሆነውን መሬት ያለብክነት ለመምራትና ለመጠቀም እየተሰራ ነው – የባስኬቶ ዞን አስተዳደር
በጎፋ ዞን ጋልማ ከተማ በ2019 በጀት ዓመት ከ18 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል ለመፍጠር መታቀዱ ተገለፀ
የሀድያ ብሔር የዘመን መለወጫ “ያሆዴ” በዓልን ለማክበር በቂ ዝግጅት መደረጉ ተገለጸ