በክልሉ የሚከናውኑ የመሠረተ ልማት ሥራዎች የሕብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ሊሆኑ እንደሚገባ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ገለፁ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ አለማየሁ ባውዲ የተመራው የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎች አባላት በክልሉ መስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ቢሮ በደቡብ ኦሞ ዞን የተሠሩ የልማት ሥራዎችን ምልከታ እያደረጉ ይገኛሉ።
የቋሚ ኮሚቴዎች አባላት በሁለት ተከታታይ ቀናት በሚኖራቸው ቆይታ የእንስሳት መሸጫ ገበያ ማዕከላትን፣ የመኖና መስኖ ልማት ሥራዎችን፣ የተማሪዎች ሆስቴል አገልግሎትን፣ ንጹህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦትና ሌሎች የአርብቶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተሠሩ መሠረተ ልማቶችን ምልከታ ያደርጋሉ ተብሎም ይጠበቃል።
ዘጋቢ፡ ተመስገን አሰፋ – ከጂንካ ጣቢያችን

More Stories
የአርብቶ አደሩን ማህበረሰብ በመንገድ መሠረተ ልማት ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መሰኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ አሰታወቀ
ሳውላ ከተማን ለኢንቨስትመንትና ለቱሪዝም ምቹ የማድረግ የ5 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት ሥራ እየተካሄደ ነው
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የቱሪዝም ሀብቶችን በማልማትና ሰላምን በማጽናት ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የማድረግ ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል