የአፈርና ውሃ ጥበቃ በማጠናከር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ መስራት እንደሚገባ ተገለፀ
ሀዋሳ፡ ጥር 18/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) የአፈርና ውሃ ጥበቃ በማጠናከር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ መሥራት እንደሚገባ የሀዲያ ዞን ግብርና መምሪያ አሳሰበ።
“የተቀናጀ የግብርና ልማት ጥረት ለቤተሰብ ብልጽግና ስኬት” በሚል መሪ ቃል የሀድያ ዞን ግብርና መምሪያ የ2018 የተፋሰስ ሥራ ማስጀመሪያና የበልግ እርሻ የነቅናቄ መድረክ በአመካ ወረዳ ኦሎልቾ ቀበሌ እየተካሄ ነው።
በዚህም በዞኑ በተጀመረው የተፋሰስ ልማት ሥራ ከ69 ሺ ሄክታር ማሳ በላይ ለማልማት እቅድ መያዙም ተመላክቷል።
በመርሃ ግብሩ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማቴዎስ አኒዮ፣ የሀዲያ ዞን ዋና የመንግሥት ተጠሪና የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታምራት ግዛው፣ የዞኑ ግብርና መምሪያ ኃላፊ ዶ/ር ሀብታሙ ታደሠ፣ የሁሉም ወረዳዎች አስተዳዳሪዎችና የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊዎችና የከተማ አስተዳደር ከንቲባዎችና ጥሪ የተደረገለቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ: ኤልያስ ኤርሶ – ከሆሳዕና ጣቢያችን

More Stories
የአርብቶ አደሩን ማህበረሰብ በመንገድ መሠረተ ልማት ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መሰኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ አሰታወቀ
ሳውላ ከተማን ለኢንቨስትመንትና ለቱሪዝም ምቹ የማድረግ የ5 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት ሥራ እየተካሄደ ነው
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የቱሪዝም ሀብቶችን በማልማትና ሰላምን በማጽናት ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የማድረግ ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል