ቼልሲ፣አስቶንቪላ እና ፎረስት ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ

ቼልሲ፣አስቶንቪላ እና ፎረስት ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ

በ23ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ቼልሲ፣አስቶንቪላ እና ኖቲንግሃም ፎረስት ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል።

በለንደን ደርቢ ከሜዳው ውጪ ከክርስቲያል ፓላስ ጋር የተጫወተው ቼልሲ 3ለ1 አሸንፏል።

ለቼልሲ የማሸነፊያ ግቦችን ኤስታቫኦ ዊሊያም፣ጆኣ ፔድሮ እና ኤንዞ ፈርናንዴዝ(ፍ.ቅ.ም) የማሸነፊያ ግቦችን አስገኝተዋል።

ክርስቲያል ፓላስን ከሽንፈት ያልታደገችውን ግብ ሪቻርድስ አስቆጥሯል።

አዲሱ የቼልሲ አሰልጣኝ ሊያም ሮሴንየር የመጀመሪያቸውን ሁለት የሊግ ጨዋታቸውን ማሸነፍ ችለዋል።

ፓላስ በአንፃሩ በፕሪሚዬር ሊጉ ያለፉትን 8 ተከታታይ ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም።

ሁለተኛ ተከታታይ ድሉን ያሳካው ቼልሲ ነጥቡን 37 በማድረስ 4ኛ ደረጃን ሲይዝ ፓላስ በ28 ነጥብ 15ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

 በተመሳሳይ ከሜዳው ውጪ ከኒውካስል ጋር የተጫወተው አስቶንቪላ 2 ለ 0 አሸንፏል።

ለአስቶንቪላ የማሸነፊያ ግቦችን ኤሚሊያኖ ቡንዲያ እና ኦሌ ዋትኪንስ ከመረብ አሳርፈዋል።

የአሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬው ቡድን አስቶንቪላ ኒውካስልን በሴንት ጀምስ ፓርክ ስታዲየም ከ 21 ዓመታት በኋላ ማሸነፍ ችሏል።

ከኤቨርተኑ ሽንፈት ማገገም የቻለው አስቶንቪላ ነጥቡን 23 በማድረስ 3ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ኖቲንግሃም ፎረስትም ከሜዳው ውጪ ብሬንትፎርድን 2 ለ 0 በሆነ ተመሳሳይ ውጤት አሸንፏል።

ኢጎር ጄሱስ እና ታዮ አዎኒዪ የፎረስትን የማሸነፊያ ግቦች አስቆጥረዋል።

ፕሪሚዬር ሊጉ ምሽት ላይ መካሄዱን ሲቀጥል ከ1 ሰዓት ከ30 ጀምሮ አርሰናል ከማንቸስተር ዩናይትድ ተጠባቂ ጨዋታ ያደርጋሉ።

ዘጋቢ ፡ ሙሉቀን ባሳ