ፓትሪክ ዶርጉ ለ10 ሳምንታት ያኽል ከሜዳ ሊርቅ ነው
የማንቸስተር ዩናይትዱ የመስመር ተመላላሽ ፓትሪክ በጉዳት ምክንያት ለ10 ሳምንታት ያኽል ከሜዳ ሊርቅ እንደሚችል ተገልጿል።
ፓትሪክ ዶርጉ ማንቸስተር ዩናይትድ አርሰናልን 3ለ2 በረታበት እና ተጫዋቹ ጎል ባስቆጠረበት ጨዋታ ጉዳት አጋጥሞት ተቀይሮ መውጣቱ ይታወሳል።
በጉዳቱ ምክንያት ዴንማርካዊው ተጫዋች ቢያንስ ለሁለት ወራት ከሜዳ ሊርቅ እንደሚችል ዘ አትሌቲክ አስነብቧል።
የፓትሪክ ዶርጉ መጎዳት ከአሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ስንብት ወዲህ አስደናቂ ክህሎቱን በማሳየት ላይ ለሚገኘው ተጫዋች እና ለክለቡ ጥሩ ዜና አይደለም።
የ22 ዓመት ፓትሪክ ዶርጉ ዩናይትድ በፕሪሚዬር ሊጉ ባለፉት ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎች መሪውን አርሰናልን እና ማንቸስተር ሲቲን ሲያሸንፍ ጎል ማስቆጠሩ ይታወሳል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
“ማንቸስተር ሲቲ በዚህ አጨዋወት ሊጉን ማሸነፍ አይችልም”ፖል ሜርሰን
ኬሮድ የጎዳና ላይ ሩጫ ህዝብ ለህዝብ የሚያስተሳስርና አንድነታችንን ይበልጥ የምናጠናክርበት በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አስታወቀ
ከ1500 በላይ ኤሊት አትሌቶች የሚሳተፉበት 6ኛው ዙር የኬሮድ የ15 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በወልቂጤ ከተማ ተጀመረ