በበጀት አመቱ በ71 ሺህ 219 መዛግብት ላይ ውሳኔ መስጠት መቻሉ ተገለጸ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የ2018 በጀት አመት አፈፃፀም ለክልሉ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ጉበኤ ቀርቧል።
ሪፖርቱን ያቀረቡት የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ኤርሲኖ አቡሬ እንዳሉት፤ በበጀት አመቱ በ71 ሺህ 219 የወንጀልና የፍትሃብሄር መዛግብት ላይ ውሳኔ መስጠት ተችሏል።
በበጀት አመቱ ካለፈው አመት የተላለፈ የወንጀል 581 እና የፍትሐብሔር 1 ሺህ 469 በድምሩ 2 ሺህ 50 መዛግብት እንደቀረበ ገልፀዋል።
ፕሬዝደንቱ አያይዘውም በበጀት አመቱ አዲስ የቀረበው የፍትሐብሔር 44 ሺህ 845 የወንጀል 26 ሺህ 391 በድምሩ 73 ሺህ 217 መዛግብት እንደቀረበ በሪፖርታቸው አብራርተዋል።
በበጀት አመቱ ከቀረቡ 73 ሺህ 217 የወንጀልና የፍትሐብሔር መዛግብት ውስጥ በ71 ሺህ 219 መዛግብት ላይ ውሳኔ መስጠት መቻሉን አብራርተዋል።
ይህም ከባለፈው በጀት አመት ጋር ሲነፃፀር 3 በመቶ ብልጫ እንዳለው ፕሬዝዳንቱ ገልፀዋል።
ዘጋቢ፡ መለሰች ዘለቀ

More Stories
መሳላ የሕዝቦችን ትስስር፣ አንድነትና መከባበርን የሚያጎለብት ታላቅ በዓል ነው – የተለያዩ ብሔር ብሔረሰብ ተወካዮች
የሀድያ ብሔር ዘመን መለወጫ “ያሆዴ” በዓል ከብሔሩ ዘመን መለወጫነት ባሻገር የሚያበረክተው ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ የጎላ ነው – የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማቴዎስ አኒዮ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) የ”ያሆዴ” በዓልን ስናከብር ስለ ሀገራችን ልማትና ስለ ህዝባችን አብሮነት የበለጠ የምንተጋበት ወቅት ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል