የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለ2019 በጀት ዓመት 67 ቢሊየን ብር በጀት አጸደቀ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ጉባኤ በወልቂጤ ከተማ እየተካሔደ ነው፡፡
የዘንድሮው በጀት ከ2018 በጀት ጋር ሲነፃፀር የ25 በመቶ ብልጫ እንዳለውም ተገልጿል።
የፌደራል መንግስት ጥቅል የበጀት ድጋፍ 31 ቢሊዮን 748 ሚሊዮን 169 ሺህ 478 ብር ሲሆን ይህም ከ2018 በጀት ጋር ሲነፃፀር የ19 ነጥብ 58 በመቶ ብልጫ እንዳለው ተጠቁሟል።
በክልሉ ከተለያዩ የገቢ ምንጮች ለመሰብሰብ የታቀደው 35 ቢሊዮን 251 ሚሊዮን 830 ሺህ 522 ብር ሲሆን ይህም ከ2018 ዕቅድ ጋር ሲነፃፀር የ30 ነጥብ 55 በመቶ ብልጫ አለው።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሁለተኛ ቀን ውሎው ለ2019 በጀት ዓመት የቀረበለትን ረቂቅ በጀት ተመልክቶ 67 ቢሊየን ብር በጀት አጽድቋል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን መሰረተ ልማትና የመንግስት ሀብት ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ታመነ ገብሬ የ2019 በጀት አመት ረቂቅ በጀትን ለምክር ቤቱ በዝርዝር አቅርበዋል።
በጀቱ ከፌደራል መንግስት ግምጃ ቤት፣ ከውጭ እርዳታ እና የዘላቂ ልማት ግቦች 31 ቢሊየን 748 ሚሊየን 169 ሺ 478 ብር መሆኑን አቶ ታመነ በማብራሪያቸው ገልጸዋል።
በክልሉ ከመደበኛ ገቢ፣ ከመስሪያ ቤቶች የውስጥ ገቢ፣ ከጤና ተቋማት ገቢ፣ ከማዘጋጃ ቤት እና ከትምህርት ቤቶች ገቢ በጥቅሉ 35 ቢሊየን 251 ሚሊየን 830 ሺ 522 ብር መሆኑን አቶ ታመነ ጠቁመዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ዘይቱና ኢብራሂም ለ2019 ስራ ላይ የሚውል ረቂቅ የበጀት አዋጅ መግለጫ ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የ2019 ረቂቅ በጀት አዋጅ 67 ቢሊዮን ሆኖ በአንድ ድምጸ ተአቅቦ ፀድቋል።
ዘጋቢ፡ መለሰች ዘለቀ

More Stories
የጉራጌ ማህበረሰብ ባህላዊ እሴቶች ሳይበረዙ ለትውልድ ለማስተላለፍ የኪነ ጥበብ ዘርፉን በማጠናከር ላይ እንደሚገኝ የጉራጌ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ አስታወቀ
“እየተከልን ያለነው ችግኝ ብቻ ሳይሆን የምግብ ሉዓላዊነታችንን ጭምር ነው” – የኢፌዲሪ ውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ(ዶ/ር)
የተመጣጠነ የአመጋገብ ሥርዓትን መከተል ጤናማ ትውልድ እንዲፈጠር የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ