ፌስቲቫሉ ከወድድርም ባለፈ የአብሮነታችንን ዕሴት ያጎለበተ ነበር ሲሉ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የታዳጊዎች ምዘናና የባህል ስፖርት ውድድር ፌስቲቫል ተሳታፊዎች ተናገሩ
በየደረጃው ያሉት አካላት ዘርፉን በማጠናከር የእርስበርስ ትስስር እንዲጎለብት እንዲሰሩ የክልሉ ባህልና ስፖርት ቢሮ አሳስበዋል።
በክልሉ የሚገኙትን ህዝብ ያሳተፈ የባህል ስፖርት ውድድር በዲላ ከተማ አስተዳደር ለተከታታይ ስምንት ቀናት ሲካሄድ ቆይቶ መቋጫውን አግኝቷል።
ተወዳዳሪዎችም ፌስቲቫሉ ከውድድር ባለፈ የአብሮነትን ዕሴት በማጎልበት እርስ በርስ እንዲተዋወቁ ምቹ አጋጣሚ የፈጠረ እንደነበረ ነዉ በደቡብ ሬዲዮና ቴለቪዥን ለይርጋጨፌ ቅርጫንፍ ሃሳባቸውን ያጋሩት።
ተወዳዳሪ አቶ አረጋ አበራ ከጋሞ ዞንና ሠላማዊት መሠለ ከዲላ ከተማ አስተዳደር እንደገለጹት በውድድሩ ባዩት በርካታ ባህላዊ ስፖርት ውድድር መደመማቸውን ገልጸው እነዚህ ስፖርቶች ከሃገር አልፈው የኦሎምፒክ ስፖርት አካል ሆነው ማየት ምኞታቸው እንደሆነም አስረድተዋል።
የዉድድሩ ተሳታፊ በመሆናቸው ትልቅ የደስታ ስሜት በውስጣቸው እንደፈጠረ የገለፁት ተወዳዳሪዎቹ ከወድድርም ባለፈ የአብሮነታችንን ዕሴት ያጎለበተ ነበር ሲሉም ተናግረዋል።
በክልሉ ባህልና ስፖርት ቢሮ የባህል ስፖርት ከፍተኛ ባለሙያ አቶ መስፍን ፋንቱ በበኩላቸው መሰል ዉድድር ክልሉ እንደ አዲስ ከተደራጀ ወዲህ ለሶስተኛ ጊዜ መካሄዱን ጠቅሰው የአብሮነትን ዕሴት ለማጠናከር የሚተገበሩ ተግባራትን በእጅጉ እየረዳ እንደሚገኝም አስገንዝበዋል።
ይህ ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ባለቤት የሆነውን የማህበረሰቡን ዕሴት መጠበቅና መንከባከብ አማራጭ ያለው ጉዳይ አይደለም ያሉት አቶ መስፍን፥ በየደረጃው ያሉት አካላት ዘርፉን በማጠናከር የእርስበርስ ትስስር እንዲጎለብት እንዲሰሩም አሳስበዋል።
ዘጋቢ፡ አማኑኤል ትዕግስቱ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን

More Stories
“ማንቸስተር ሲቲ በዚህ አጨዋወት ሊጉን ማሸነፍ አይችልም”ፖል ሜርሰን
ኬሮድ የጎዳና ላይ ሩጫ ህዝብ ለህዝብ የሚያስተሳስርና አንድነታችንን ይበልጥ የምናጠናክርበት በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አስታወቀ
ከ1500 በላይ ኤሊት አትሌቶች የሚሳተፉበት 6ኛው ዙር የኬሮድ የ15 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በወልቂጤ ከተማ ተጀመረ