በዞኑ የሚገኙ የተፈጥሮ ፀጋዎችና እምቅ ባህሎችን በማልማት ሀገሪቱ የጀመረችውን የቱሪዝም ሪፎርም እውን ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ

በዞኑ የሚገኙ የተፈጥሮ ፀጋዎችና እምቅ ባህሎችን በማልማት ሀገሪቱ የጀመረችውን የቱሪዝም ሪፎርም እውን ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ

ሀዋሳ፡ ጥር 17/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) በዞኑ የሚገኙ የተፈጥሮ ፀጋዎችና እምቅ ባህሎችን በማልማት ሀገሪቱ የጀመረችውን የቱሪዝም ሪፎርም እውን ማድረግ እንደሚገባ የደቡብ ኢትዮጵያ ብሄረሰቦች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ አዳማ ትንጳዬ ገለጹ፡፡

‎አፈ-ጉባኤው ይህንን ያሉት ለ7ኛ ጊዜ እየተከበረ ባለው የጋርዱላ ህዝቦች የዘመን መለወጫ “የሀይሶት ህርባ” እና ፊላ ፌስቲቫል ላይ ነው።

‎”የባህል ልማታችን ለብልፅግናችን” በሚል መሪ ቃል በዞኑ ለ7ኛው ጊዜ እየተገበረ ያለው የሀይሶት ህርባ ዘመን መለወጫ በዓል በድምቀት እየተከበረ ነው።

በዓሉ በሀይማኖት አባቶች ፀሎትና ቡራኬ ነው የተጀመረው ።

‎በበዓሉ ተገኝተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የጊዶሌ ከተማ ከንቲባ አቶ አሸናፊ ታዬ፥ በጋርዱላ ህዝቦች የዘመን መለወጫ “የሀይሶት ህርባ” እና ፊላ ፌስቲቫል በአካባቢው የሚገኙ 4 ነባር ብሔረሰቦች በጋራ ደምቀው በአብሮነት የሚያከብሩበት ታላቅ በዓል ነው ብለዋል።

‎ፊላ ባለ 7 ኖታ የትንፋሽ ሙዚቃ መሳሪያ መሆኑን የተናገሩት ከንቲባው በዓለም ታሪክ እንዲመዘገብ በትኩረት እየተሰራ ሲሆን በዚህ ውስጥ አንድነታችንን በማጠናከር ከግጭት አዙሪት በመውጣት አካባቢውን የሠላምና የልማት ተምሳሌት ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ነው።

‎በጋርዱላ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ግኑኝነት ኪታሞ ባስተላለፉት መልዕክት “የባህል ልማታችን ለብልፅግናችን” በሚል መሪ ቃል በዞኑ ለ7ኛው ጊዜ እየተገበረ ያለው የሀይሶት ህርባ ዘመን መለወጫ የአብሮነታችንንና ሁለንተናዊ ሠላማችንን የምናፀናበት በዓል እንደሆነ አስገንዝበዋል ።

‎በዞኑ በ4ቱም ብሄረሰቦች ዘንድ የሚገኙ እምቅ ሀብቶችና የተፈጥሮ ዕሴቶችን በማልማት ለሠላም ግንባታችን ማዋል ይገባል ነው ያሉት ዋና አስተዳዳሪ ።

‎በመርሐ ግብሩን የከፈቱት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የብሄረሰቦች ም/ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ አዳማ ትንጳዬ በዞኑ የሚገኙ የተፈጥሮ ፀጋዎችና እምቅ ባህሎችን በማስተዋወቅ ሀገሪቱ የጀመረችውን ሀገር በቀል የቱሪዝም ሪፎሪም ስኬታማነት በትኩረት ልንሰራ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።

‎በመርሀ ግብሩ የተለያዩ ጥናታዊ ፅሐፎች ቀርበው ውይይት እየተደረገበት ይገኛል።

‎ዘጋቢ ፡ እንጃ ገልሲሞ – ከአርባምንጭ ጣቢያችን