ችግር ፈቺ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራዎችን በመስራታቸው ዘርፈ ብዙ ጠቄሜታ ማግኘታቸውን የአርባምንጭ ፖሊ ቴክኒክና ሳታላይት ኮሌጅ ተማሪዎችና መምህራን ገለፁ

ችግር ፈቺ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራዎችን በመስራታቸው ዘርፈ ብዙ ጠቄሜታ ማግኘታቸውን የአርባምንጭ ፖሊ ቴክኒክና ሳታላይት ኮሌጅ ተማሪዎችና መምህራን ገለፁ

‎ኮሌጁ በቴክኖሎጂ ፈጠራዎችና በሌሎች የሙያ መስኮች ስልጠናዎችን በመስጠት ብቁ ስልጣኞችን በማፍራት ረገድ ሰፊ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

‎ኮሌጁ የመቶ ቀናት እቅድን ለማሳካት ተማሪዎችንና መምህራንን በማስተባበር እየሰራ እንደሆነም ተጠቁሟል።

‎አሰልጣኝ መስቀሉ ኡርማሌና ዳንኤል ተሰፋዬ በአርባምንጭ ፖሊ ቴከኒክና ሳታላይተት ኮሌጅ የሁለተኛ ዓመት የብረታብረትና የእንጨት ስራ ሰልጣኞች ሲሆኑ በተቋሙ የተለያዩ የቴክኖሎጂ የፈጠራ ስራዎችን እየሰሩ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

‎አክለውም ከተቋሙ ከሚያገኙት ስልጠና በርካታ የፈጠራ ስራዎች እውቀት ማግኘታቸውን ተናግረው በቀጣይ ወደ አካባቢያቸው ሲመለሱ ከራሳቸዉ አልፈው ለአካባቢውና ለወጣቶች የሰራ እድልን ለመፍጠር ስልጠናዉ አይነተኛ ሚና እንዳለዉ ጠቁመዋል።

‎በቴክኖሉጂ ፈጠራና የስልጠና ሂደት ከማስተማር ባሻገረ በተግባር የተደገፈ ችግር ፈቺ የሆኑ የተለያዩ ፈጠራዎችን መሰራታቸውን የተናገሩት መምህርና ቴክኖሎጂስት ጥበቡ ዘነበ፥ የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ ማሸን በመፍጠር ለህብረተሰቡ ተደራሸ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

በአሰልጣኞችና በሰልጣኝ ተማሪዎች መካከል የእውቀት ሽግግር ከመፍጠር ባሻገር በስድስት የስልጠና ዘርፎች የተለያዩ ችግር ፈቺ የሆኑ የፈጠራ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ ያስረዱት የኮሌጁ ምክትል ዲኒና የቴክኖሎጂ ሸግግር እንዱስተሪ ኤክስቴንሽን ዋና ስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ወርቅነህ ኃይለ ሚካኤል ናቸው፡፡

‎ሀገራችን በ2ዐ3ዐ እውን ለማድረግ ያቀደችዉን የቴክኖሎጂ ዓለም ከግብ ለማድረስ በሚደረገው ርብርብ በእውቀት፣ ክህሎትና በብቃት የሰለጠነ የሰው ሃይል ማፍራት ሚናዉ የላቀ እንዳሆነ የተናገሩት የአርባምንጭ ፖሊ ቴክኒክና ሳታላይት ኮሌጅ ዋና ዲኒ አቶ በዛብህ ባርዛ ናቸው፡፡

‎ወጣቶችን የስራ ፈጠራ ባለቤት ለማድረግ ምርትና ምርታማነትን ከመጨመር አኳያ ተቋሙ የተሻለ ስራ ለመስራት ቁርጠኛ እንደሆነም አመላክተዋል፡፡

‎ዘጋቢ፡ ስምረት አስማማው – ከአርባምንጭ ጣቢያችን