ሀዋሳ፡ ሚያዚያ 20/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) ኢትዮጵያን ለዘመናት ከቆየችበት ቁስል ለማላቀቅ ባለፉት የለውጥ አመታት በርካታ ፖለቲካዊ ተግባራት ማከናወኑን መቻሉን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ገብረመስቀል ጫላ ገለጹ።
የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ቤት የሴቶች ክንፍ የድጋፍ ስልፍ እና ለ7ኛ ጠቅላላ ምርጫ ሴት እጩዎችን የማስተዋወቅ መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ ተካሂዷል።
ኢትዮጵያን ለዘመናት ከቆየችበት ቁስል ለማላቀቅ ባለፉት የለውጥ አመታት በፓርቲዉ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን የገለጹት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ገብረመስቀል ጫላ፥ የህዳሴ ግድብን ጨምሮ ለሀገር ኢኮኖሚ ከፍተኛ ሚና ያላቸው ፕሮጀክቶች መገንባታቸዉን ለአብነት አንስተዋል።
ሰዉ ተኮር በሆኑ ስራዎች አመርቂ ውጤት መጥቷል ያሉት ኃላፊዉ፥ አካታች በሆነ መልኩ ስራዎች መሰራታቸውን አመላክተዋል።
በመጪው አምስት ዓመታት የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመምራት ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።
ፓርቲዉ ለሴቶች የሰጠዉ ክብር እንዲሁም እድል ለሀገር የኢኮኖሚ እድገት መሰረት ነዉ ያሉት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ም/ል አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ወላይቴ ቢቶ፥ ሴቶች አቅማቸውን አጉልተው እንዲያወጡ በማድረግ በተለያዩ ዘርፎች ከራሳቸው አልፈው ለሌላ መትረፍ እዲችሉ ከማድረግ አኳያ በአመራርነት እንዲያገለግሉ ብልጽግና ፓርቲ እድል መፍጠሩን ገልጸዋል።
የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ቅ/ጽቤት ሀላፊ ወ/ሮ እቴነሽ በየነ ብልጽግና ፓርቲ ለሴቶች በሰጠው ትኩረት እንዲሁም በተፈጠረዉ ምቹ ሁኔታ በመጠቀም ሀገር የጀመረችውን የልማት ጉዞ ከግብ ለማድረስ ሴቶች ሚናቸዉን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።
የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ እታገኝ ኃ/ማርያም በበኩላቸው ባለፉት አመታት በብልፅግና ፓርቲ መሪነት የተመዘገቡ ስኬቶችን በዝርዝር አስቀምጠዉ፥ ለሴቶች ፓርቲው ልዩ ትኩረት ይሰጣል ብለዋል።
በመድረኩ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት አመራሮች፣ የብልፅግና ፓርቲ ሴት የሕዝብ ተወካዮችና የክልል ምክር ቤት ዕጩዎች፣ የሴቶች ክንፍ አባላትና አመራሮች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳታፊ ሆነዋል።
ዘጋቢ፡ ባዬሽ ጉልላት

More Stories
ችግር ፈቺ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራዎችን በመስራታቸው ዘርፈ ብዙ ጠቄሜታ ማግኘታቸውን የአርባምንጭ ፖሊ ቴክኒክና ሳታላይት ኮሌጅ ተማሪዎችና መምህራን ገለፁ
ለሰባተኛ ጠቅላላ ምርጫ ሴት እጩዋችን የማስተዋወቅ መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተካሄደ ነዉ
ለክብሩ የሚጫወት ታጋይ