በከተማ ያለውን ህገወጥ የንግድ ስርዓት እና ኮንትሮባንድን በማስቀረት ህጋዊ ነጋዴዎችን የመደገፍ እና የማበረታታት ስራ እንደሚሰራ ተገለጸ
ሀዋሳ፡ ሚያዚያ 22/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ህገወጥ የንግድ ስርዓት እና ኮንትሮባንድን በማስቀረት ህጋዊ ነጋዴዎችን የመደገፍ እና የማበረታታት ስራ እንደሚሰራ የከተማው ከንቲባ ኢንጅነር ሰለሞን ለዊ ተናገሩ።
“ሁለንተናዊ ብልጽግና የማህበረሰቡ ሚና” በሚል ከሚዛን አማን ከተማ ንግድ ማህበረሰብ ጋር የውይይት መድረክ ተካሂዷል።
ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር የውይይት መድረክ በተካሄደበት ወቅት የተገኙት የሚዛን አማን ከተማ ከንቲባ ኢንጅነር ሰለሞን ለዊ እንደተናገሩት በከተማው እየተመዘገበ ላለው ፈጣን እድገት፥ የንግዱ ማህበረሰብ ድርሻ ትልቅ መሆኑንም ጠቁመዋል።
በከተማው በተለይም የታማኝ ግብር ከፋዮች ውጤት ትልቅ መሆኑን ጠቁመው፥ ለዚህም በተከናወኑ የከተማ መልሶ ግንባታ እና የኮሪደር ልማት ተግባራት አማላካች እንደሆነ ተናግረው፥ የሞዴል ትምህርት ቤቶች ግንባታ፣ የሰላም እና ጸጥታ ተግባራቶች በተለይም ከለውጡ በኋላ በብልጽግና የተገኙ ውጤቶች መሆናቸውን ኢንጅነር ሰለሞን አስረድተዋል።
የንግዱን አከባቢ ምቹ ከማድረግ ባለፈ ህገወጥ እና የኮንትሮባንድ ንግድ ቁጥጥር ተግባራትን በማጠናከር የማያዳግም እርምጃ እንደሚወሰድ ጠቁመዋው፥ የንግዱ ማህበረሰብ ከከተማ አስተዳደሩ ጎን መቆም ይጠበቅበታል ብለዋል።
ከፊታችን የሚካሄደው ሰባተኛ ጠቅላላ ምርጫ የንግዱ ማህበረሰብ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ዲሞክራሲያዊ መብታቸውን እንዲጠቀሙ ኢንጅነር ሰለሞን ለዊ ጥሪ አቅርበዋል።
የከተማ አስተዳደሩ ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር እየተካሄደ ባለው ውይይት የከተማ ኢንዱስትሪ እና ንግድ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌታቸው መለሰ የውይይት ሰነድ የቀረበ ሲሆን፥ በከተማው ከስድስት ሺ በላይ በተለያዩ የንግድ ዘርፍ የተሰማሩ ነጋዴዎች መኖራቸውን ጠቁመዋል።
ባለፉት ዘጠኝ ወራት 875 ሚሊዬን ብር ገቢ መሰብሰቡንም ጠቁመው፥ ይህም በከተማው ለተከናወኑት የልማት ተግባራት ማዋል መቻሉን ገልጸው፥ የተጀመረውን የልማት ስራ ለማስቀጠል የንግዱ ማህበረሰብ ከከተማ አስተዳደሩ ጎን መቆም ይጠበቅበታልም ብለዋል።
የንግዱ ማህበረሰብ በቀረበው ሰነድ ላይ ውይይት እያደረገ ይገኛል።
ዘጋቢ: አብዮት በቀለ – ከሚዛን ጣቢያችን

More Stories
የብራይት ፕሮጀክት የሴቶችንና ህፃናትን የስራ ጫና ከማቃለል ባሻገር የንፁህ መጠጥ ውሀ ተደራሽነት ላይ የሚመታይ ተግባር ማከናወኑን የጋሞ ዞን ውሀና ኢነርጂ መምሪያ አስታወቀ
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ጥናታቸው በተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች ላይ ያተኮረ የማረጋገጫ ወርክሾፕ እና የርክክብ መርሃ ግብር እያካሄደ ይገኛል
የማህበረሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመፍታት የቤት ልማት አቅርቦት ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ