ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) በዳውሮ ዞን ባሌ ከተማ አስተዳደር ሶዶ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን መርቀው ከፈቱ
ሀዋሳ፡ ሚያዝያ 22/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) በዳውሮ ዞን ባሌ ከተማ አስተዳደር ሶዶ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን መርቀው ከፍተዋል፡፡
ትምህርት ቤቱ በሀገር ደረጃ ለሞዴል ትምህርት ቤቶች ግንባታ በተያዘው ኢኒሼቲቪ መነሻ የተተገበረ መሆኑም በዚሁ ወቅት ተመላክቷል።
የባሌ ከተማ አስተዳደር ከተዋቀረ በኋላ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢኒሼቲቪ የተገነባ መሆኑ ተገልጿል።
ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቱ በአካባቢው ማህበረሰብና በጎ አድራጎት ከ14 ሚሊዮን ብር በላይ መገንባቱም ተመላክቷል።
ትምህርት ቤቱ በአካባቢው መገንባቱ ለህጻናት ክህሎት ማበልጸጊያ ያለው ድርሻ የላቀ መሆኑ ተጠቁሟል።
በቀጣይ ሀገር ተረካቢ ትውልድ እንዲፈጠር አበርክቶው የላቀ ነውም ተብሏል።
ዘጋቢ፡ አዲስዓለም ታዬ – ከዋካ ጣቢያችን

More Stories
ምክር ቤቱ በ2018 በጀት አመት ሪፖርት እና የ2019 ጠቋሚ እቅድ ላይ ተወያይቶ በሙሉ ድምጽ አጸደቀ
በበጀት አመቱ ከ26 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰብስቧል – ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)
በበጀት ዓመቱ ከ379 ሺ በላይ ዜጎች የስራ እድል ተፈጥሮላቸዋል – ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)