በህዝባዊ አንድነት የተጀመሩት የልማት ስራዎች ቀጣይነት እንዲኖረው ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ ይገባል
ሀዋሳ፡ ጥር 17/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) በህዝባዊ አንድነት የተጀመሩት የልማት ስራዎች ቀጣይነት እንዲኖረው ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባ የጌዴኦ ዞን አስተዳደር አስታወቀ፡፡
ይህም የተገለፀው የተለያዩ ፕሮጀክቶች በጌዴኦ ዞን ገደብ ወረዳ በተመረቀበት ነው፡፡
በምረቃው መርሃግብር እንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የገደብ ወረዳ አስተዳደሪ አቶ ሲሳይ ታደሰ ፕሮጀክቶቹ የረጅም ጊዜ እቅድ ተይዞ የተጀመረ ሲሆን በነዋሪዎች፣ በመንግሥት ሰራተኞች፣ በባለሃብቶችና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት የገንዘብ ድጋፍ ተጠናቅቀው ለአገልግሎት በመብቃታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል፡፡
ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ወጥቶበት ከተመረቁት ፕሮጀክቶች 11 ሴክተር መ/ቤቶች ያቀፈ የአስተዳደር ህንፃ፣ መሰብሰቢያ አደራሽ፣ የገበሬዎች ማሰልጠኛ ማዕከል፣ የመንገድ ስራ ዶዘር መኪናና ለሌሎች የምጠቀሱ መሆናቸውን ያሳወቁት አስተዳደሪው ለዚህም ድጋፍ ያደረጉት አካላት አመስግነዋል፡፡
የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ (ዶ/ር) በምረቃው መርሃግብር ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለፁት የህብረተሰቡን የልማት ጥያቄ ለመመለስ እንደ ዞን በተጀመሩት ስራዎች ውጤት እየተመዘገበ ነው፡፡
በህዝባዊ አንድነትን የተጀመሩት የልማት ስራዎች ቀጣይነት እንዲኖረው ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ አስተዳደሪው አሳስበዋል፡፡
በምረቃ መርሃ ግብር የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ(ዶ/ር)፣ የጌዴኦ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ እንጂነር ተመስገን ጥላሁንን ጨምሮ፣ አባ ጋዳዎች፣ የዞን፣ የከተማ አስተዳደሮችና የወረዳ አስተዳደሮች የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝቷል ።
ዘጋቢ፡ ውብሸት ኃ/ማርያም – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን

More Stories
የህዝቡ የልማትና የመልካም አስተዳዳር ጥያቄዎች በዘላቂነት እንዲመለሱ ከየትኛውም ጊዜ በላይ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኧሌ ዞን ሽግግር ምክር ቤት ገለፀ
መንግስት የደን ጭፍጨፋን በመከላከል የአየር ሚዛንን ለመጠበቅ በሚያደርገው ጥረት ውስጥ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ደን፣ አካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ ቢሮ እስታውቀ
የህዝቡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመቅረፍ እንዲያስችል ዞኑ የሚያመነጨውን ገቢ በአግባቡ መሰብሰብ እንደሚገባ የጉራጌ ዞን አስተዳደር አስታወቀ