ሀዋሳ፡ ጥር 15/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) በዘንድሮ በልግ 182 ሺህ 843 ሔክታር መሬት ለማልማት ታቅዶ እየተሠራ መሆኑን የጋሞ ዞን ግብርና መምሪያ አስታወቀ፡፡
የበልግ እርሻ እንቅስቃሴ ላይ ያተኮረው ዞናዊ መድረክ በአርባ ምንጭ እየተካሔደ ነው።
በዞኑ ያሉ ምቹ የግብርና ጸጋዎችን በመጠቀም ምርት እና ምርታማነትን ለማሳደግ አየተሠራ መሆኑን የጋሞ ዞን ግብርና መምሪያ ምክትል ሀላፊ አቶ ወርቅነህ ካልሳ ተናግረዋል።
በዘንድሮ የበልግ እርሻ ለማልማት ዞናዊ ንቅናቄ መጀመሩን የተናገሩት አቶ ወርቅነህ አንድም መሬት ጾም እንዳያድር ሁሉንም አቅሞችን እንጠቀማለን ነው ያሉት።
የዞኑ ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ማጌሶ ማሾሌ፤ በዘንድሮው የበልግ እርሻ ከ34 ሚሊየን በላይ ኩንታል ምርት ለማግኘት እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
በምርት ዘመኑ 182 ሺህ 843 ሄክታር መሬት በተለያዩ ሰብሎች ለማልማት ግብ ተጥሎ በትኩረት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸው፥ ከ34 ሚሊየን በላይ ኩንታል ምርት ለማግኘት መታቀዱንም ሀላፊው አስረድተዋል።
በበልግ እርሻ ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም፣ የግብዓት አቅርቦት፣ ቅንጅታዊ አሰራሮችና ድጋፋዊ ክትትሎች ሊጠናከሩ ይገባል ያሉት የዞኑ የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ገዛኸኝ ጋሞ ናቸው።
የተለያዩ ሰብሎችን በማምረት የዞኑን ምርታማነት ለማሳደግ በትኩረት መሠራት እንዳለበት የምክክር መድረኩ ተሳታፊዎች በአስተያየታቸው አብራርተዋል።
ዘጋቢ፡ ወ/ገብርኤል ላቀው – ከአርባ ምንጭ ጣቢያችን

More Stories
የህዝቡ የልማትና የመልካም አስተዳዳር ጥያቄዎች በዘላቂነት እንዲመለሱ ከየትኛውም ጊዜ በላይ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኧሌ ዞን ሽግግር ምክር ቤት ገለፀ
መንግስት የደን ጭፍጨፋን በመከላከል የአየር ሚዛንን ለመጠበቅ በሚያደርገው ጥረት ውስጥ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ደን፣ አካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ ቢሮ እስታውቀ
የህዝቡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመቅረፍ እንዲያስችል ዞኑ የሚያመነጨውን ገቢ በአግባቡ መሰብሰብ እንደሚገባ የጉራጌ ዞን አስተዳደር አስታወቀ