መርሃግብሩን ያስጀሩት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የዲላ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃለፊ ዶክተር መሪሁን ፍቅሩ፤ መንግሥት ጀምሮ በመጨረስ መርህ በክልሉ ካሉት ስድስት ማዕከል አንዱ በሆነው በዲላ ክላስተር የሚገነባው የክልል ተቋማት ህንጻ በቅርብ ጊዜ ቢጀመርም ሥራዉ በፍጥነት እየተከናወነ እንደሚገኝ ጠቅሰዉ በግንባታው እየተሳተፉ ያሉትን አካላት ሁሉ አመሰግነዋለሁ።
ግንባታዉ በአጭር ጊዜ ተጠናቆ ወደ ሥራ ለመግባት ትኩረት ሰጥተዉ እየሰሩ እንደሚገኙ የተናገሩት ኃላፊው ለዚህ አላማ ስኬት ሁሉም የድርሻዉን እንዲወጣ አሳስበዋል።
እንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የዲላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ዶክተር መስፍን ደምሴ፤ መንግሥት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት በህዝብ ፍላጎት መነሻ እንዲደራጅ ካደረገ ወዲህ በርካታ የልማትና የመልካም አስተዳር ጥያቄ እየመለሰ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
መንግሥት ዜጎች የሚያነሱትን ፍትሃዊ አገልግሎት ጥያቄ ለመመለስና አገልግሉቱን በሁሉም አካባቢ ተደራሽ ለማድረግም ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው።
የጌዴኦ ዞን አስተዳዳሪ ዶክተር ዝናቡ ወልዴ፤ ክልሉ ከተደራጀ ወዲህ ከተሞች እኩል እንዲያድጉ ያለዉን ቁርጠኝነት እያዩ እንደሚገኙ ጠቅሰዉ ግንባታው እስከሚጠናቀቅ ዞኑ የሚጠበቅበትን ሁሉ ለመወጣት ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።
ለህንጻዉ ግንባታ ከ4 መቶ ሚሊየን ብር በላይ ወጪ እንደሚደረግ የተገለጸ ሲሆን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የዲላ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር መሪሁን ፍቅሩ፣ ሌሎች የክልል፣ የዞንና ወረዳ አመራሮች በተገኙበት የመሠረት ድጋይ ተቀምጧል።
ዘጋቢ: አማኑኤል ትዕግስቱ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን

More Stories
በከምባታ ዞን ሺንሽቾ ከተማ አስተዳደር የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርአት (E-LMIS) ምዝገባ በይፋ መጀመሩን የከተማው ኢንተርፕራይዝና ሥራ ዕድል ፈጠራ ጽህፈት ቤት አስታወቀ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሆሳዕና ከተማ ሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ.ም በተከሰተው ድንገተኛ የእሳት አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ ተደረገ
ህብረተሰቡ የኤሌክትሪክ መስመሮችን ጨምሮ ለእሳት አደጋ መንስኤ የሚሆኑ የመጠቀሚያ ዕቃዎችን በጥንቃቄ በመጠቀም በሰው ህይወት እና ንብረት ላይ የሚደርሰውን ጉዳት መከላከል እንደሚገባ ተገለጸ