በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የ2018 ዓ.ም የደቡብ ኦሞ ዞን የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ በሐመር ወረዳ ላላ ቀበሌ ገማ ዱካ መንደር ማንጊ ተራራ በይፋ ተጀመረ
በሥራው 50 ንዑሳ ተፋስ በሦስቱ ከፊል አርብቶ አደር ወረዳዎች የሚተገበር ሲሆን በሄክታር 16 ሺህ 99 የሚሆን መሬት እንደሚለማ የደቡብ ኦሞ ዞን ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ምንላርገው አዲሱ ገልፀዋል።
በግጦሽ ደግሞ በቁጥር 163 የሚሆን መሬት የሚከለል ሲሆን ይህም በሄክታር ሲገለጽ 16 ሺህ 928 እንደሆነም ኃላፊው ተናግረዋል።
በግጦሽ ክለላና በተፋሰስ በአጠቃላይ 7 ሺህ 145 በአፈርና ውሃ ጥበቃ በተለያዩ ስትራክቸሮች ለመተግበር ታቅዶ ወደ ተግባር መገባቱን የደቡብ ኦሞ ዞን ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ምንላርገው አዲሱ አብራርተዋል።
ዘጋቢ: ተመስገን አበራ – ከጂንካ ጣቢያችን

More Stories
የህዝቡ የልማትና የመልካም አስተዳዳር ጥያቄዎች በዘላቂነት እንዲመለሱ ከየትኛውም ጊዜ በላይ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኧሌ ዞን ሽግግር ምክር ቤት ገለፀ
መንግስት የደን ጭፍጨፋን በመከላከል የአየር ሚዛንን ለመጠበቅ በሚያደርገው ጥረት ውስጥ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ደን፣ አካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ ቢሮ እስታውቀ
የህዝቡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመቅረፍ እንዲያስችል ዞኑ የሚያመነጨውን ገቢ በአግባቡ መሰብሰብ እንደሚገባ የጉራጌ ዞን አስተዳደር አስታወቀ