ብልሹ አሰራሮችን በመታገልና ተገቢውን እርምጃ በመውሰድ የኢንቨስትመንት ዘርፍን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትኩረት መስራት ይጠበቅበታል ሲሉ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ አሳሰቡ
የዞኑ ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት መምሪያ “የኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት በማፋጠን የሃገራችንን ብልፅግና እናረጋግጣለን” በሚል መሪ ቃል አመታዊ የኢቨስትመንት ፎረምና የኢትዮጵያ ታምርት የንቅናቄ መድረክ በወልቂጤ ከተማ አካሂዷል።
የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ በዚህ ወቅት እንደገለፁት ዘላቂነት ያለው የሃገራችን ብልፅግና ማረጋገጥ የሚቻለው በኢንዱሪስትሪ ዘርፍ ላይ መስራት ሲቻል መሆኑና በዞኑም ለኢንዱስትሪ ዘርፍ ምቹ ቦታዎች ያሉ በመሆኑ በአግባቡ ማልማት ይገባል።
በዚህም ዞኑ በኢንቨስትመንቱ ዘርፍ ለሚሳተፉ አካላት ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ዝግጁ መሆኑን የተናገሩት ዋና አስተዳዳሪው፤ በዋናነት ብልሹ አሰራሮችን ፈትሾ ተገቢውን እርምጃ በመውሰድ ዘርፉን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ ሁሉም ባለድርሻ አካል የበኩሉን መወጣት ይጠበቅበታል ሲሉም አሳስበዋል።
በተጨማሪም ዞኑ የግብርናው ዘርፍ ጤታማ በመሆኑና የአሰራር ሂደቱን በአግባቡ ተርድቶ በማዘመን ምርታማነትን ይበልጥ ማሳደግ ይጠበቃል ብለዋል።
በተለይም በባለሙያ የተደገፈ ስራ በመስራት ባለሃብቶችንና አርሶአደሩን በማቀናጀት በዞኑ ያሉትን ፀጋዎች ወደ ኢንቨስትመንት ቀይሮ መሰራት እንደሚገባም አቶ ላጫ አውስተዋል።
የዞኑ ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት መምሪያ ሃላፊ ወይዘሮ አመተሩፍ ሁሴን በበኩላቸው፤ በዞኑ ለ344 አልሚ ባለሃብቶች ከ23 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ መስጠቱን ጠቁመው በዘርፉም ከ31 ሺህ በላይ ዜጎች የስራ እድል መፍጠር መቻሉን አስታውቀዋል።
ባለፉት የለውጥ አመታት የሃገራችንን ብልፅግና ለማፋጠን ባለሃብቶች የሚያበረታታና የኢንዱስትሪ ልማት ለማፋጠን የሚያስችሉ የሪፎርም ስራዎች ተግባራዊ ከተደረገ ጊዜ ጀምሮ በዞኑ በኢንቨስትመንቱ ዘርፍ ከፍተኛ መነቃቃት መፈጠሩን ገልፀዋል።
አምራች ኢንዱስትሪዎች በሙሉ አቅማቸውን እንዲያለሙ ሁኔታዎችን ከማመቻቸት ባሻገር የተጀመሩ ፕሮጀክቶች ውጤታማነታቸውን በማረጋገጥ ጤናማ እና አምራች የኢንቨስትመንት ዘርፍ እንዲስፋፋ በየደረጃው ያሉ መዋቅሮች በትኩረት መስራት እንደሚገባቸው ተናግረዋል።
የመድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ዞኑ የአምራቹ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ከመደገፍና ከማበረታታት አኳያ እያደረገው ያለውን ተግባር የሚበረታታ መሆኑን በመጠቆም፤ ለአምራች ኢንቨስተር ለስራ ማነቆ የሆኑ የመልካም አስተዳደር ችግሮች በተለይ የመብራት ዝርጋታ አለመስፋፋትና መቆራረጥ ላይ በትኩረት ሊሰራበት ይገባል በማለት ተናግረዋል።
በእውቀት የተገነባና በቴክኖሎጂ የዳበረ ስራ በመስራት በኢንቨስትመንት ዘርፍ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ተናግረዋል።
ዘጋቢ፡ እርካብነሽ ወልደማርቆስ – ከወልቂጤ ጣቢያችን

More Stories
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ዲላ ክላስተር እየተገነባ ላለው የክልል ቢሮዎች ህንጻ ግንባታ የመሠረት ድንጋይ የማስቀመጥ መርሃግብር ተካሄደ
በክልሉ ባለፉት ስድስት ወራት ከ93 ሺ በላይ የሚሆኑ ወጣቶች በተለያዩ የስራ ዘርፎች ተሰማርተው ተጠቃሚ መሆናቸውንና ከ33 ሺ በላይ የሚሆኑት ደግሞ በውጭ ሀገር የስራ ስምሪት መሰማራታቸውን የክልሉ ስራና ክህሎት ቢሮ አስታወቀ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የ2018 ዓ.ም የደቡብ ኦሞ ዞን የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ በሐመር ወረዳ ላላ ቀበሌ ገማ ዱካ መንደር ማንጊ ተራራ በይፋ ተጀመረ