በቦንጋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የትምህርት ተቋማት ጥራት አስተዳደር ሥርዓት ተጀመረ

በቦንጋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የትምህርት ተቋማት ጥራት አስተዳደር ሥርዓት ተጀመረ

ሀዋሳ፡ ጥር 14/05/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢኒስቲትዩት በቦንጋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የትምህርት ተቋማት የጥራት አስተዳደር ሥርዓት ማስጀመሩን አስታወቀ።

በትምህርት ተቋማት የጥራት አስተዳደር ሥርዓት ጽንሰ-ሀሳብ ዙሪያ ለኮሌጁ ማህበረሰብ ስልጠና ተሰጥቷል።

የትምህርት ተቋማት የጥራት አስተዳደር ሥርዓት (ISO 21001:2025) ኮሌጁን ዓለም-አቀፍ ተወዳዳሪ የሚያደርግ መርሃ-ግብር መሆኑ ተመላክቷ።

የኮሌጁ ዲን አቶ አንዱዓለም ገብረመድህን መርሃ-ግብሩ ኮሌጁን ዓለም-አቀፍ ተወዳዳሪ የሚያደርግ መሆኑን ተናግረዋል።

ኮሌጁ ብቁ እና ለስራ ዝግጁ ዜጎችን ለማፍራት በትጋት እየሰራ መሆኑን ጠቁመው፥ ይህንኑ ለማጠናከር የሚያግዝ ሥርዓት መሆኑን ገልጸዋል።

ተማሪን መሰረት ያደረገ አስተዳደር ለመፍጠርና በመረጃና ማስረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ ለመስጠት እንዲሁም ግልጽነትንና ተጠያቂነትን ለማስፈን ቁልፍ መሳሪያ ነው ብለዋል።

የዚህ ስራ መጀመር የአመራሮችን ቁርጠኝነት፣ የሰራተኞችን ተሳትፎና የሰልጣኞችኘን ተጠቃሚነት ማዕከል ያደረገ አዲስ ምዕራፍ መሆኑንም ተናግረዋል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አብይ አንደሞ (ዶ/ር) የተጀመረው አሰራር በሌሎች ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆችም በቅርቡ ይጀመራል ብለዋል።

የኮሌጁን ደረጃ በማሳደግ ዓለም-አቀፍ ተወዳዳሪ በማድረግ ሀገራዊ ተልዕኮን መወጣት ከኮሌጁ ማህበረሰብ እንደሚጠበቅ አሳስበዋል።

ኮሌጁን፣ ሰልጣኞችን እና ሰራተኞችን ዓለም-አቀፍ ተወዳዳሪ የሚያደርግ ሥርዓት መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የቢሮው ምክትልና የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ኃላፊ በረከት ወንድሙ (ዶ/ር) ናቸው።

በኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢኒስቲትዩት የስልጠናና ቴክኒክ ድጋፍ ስራ አስፈጻሚ አቶ መንግሥቱ ተፈራ የትምህርት ተቋማት ዓለም-ዓቀፍ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሚያስችል መርሃ-ግብር ነው ብለዋል።

ኮሌጁ ተወዳዳሪ እንዲሆን የትምህርት ተቋማት የጥራት አስተዳደር ሥርዓት መጀመሩ ከፍተኛ ሚና እንዳለው አመላክተዋል።

በኮሌጁ የተጀመረው ይህ አዲስ አሰራር ውጤታማ እንዲሆን በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

በአሰራሩ ላይ ከኮሌጁ ማህበረሰብ ጋር ውይይት ተደርጓል።

ዘጋቢ፡ ሀብታሙ ኃይሌ – ከቦንጋ ጣቢያችን