ወጣቶች በዞኑ የሚገኙ ጸጋዎችን ተጠቅመው የገቢ አቅማቸውን እንዲያሳድጉ እየተደረገ ያለው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ገለጸ
ለማህበራት የተሰራጨውን የገንዘብ ብድር አሟጦ በመሰብሰብ ለአዳዲስ ማህበራት የስራ እድል ለመፍጠር ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጀት እየሰራ እንደሚገኝ የዞኑ ስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት መምሪያ አስታውቋል።
በጉራጌ ዞን ምክር ቤት የኢኮኖሚ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ጠጄ ደነቀ፤ የስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት መምሪያ ከስራ አጥ ወጣቶች ልየታ ጀምሮ እስከ ስምሪት የወጣቶች ተጠቃሚነት ለማሻሻል እያከናወናቸው የሚገኙ ስራዎች በመስክ በሪፖርትና በአካል ማረጋገጣቸውን ጠቅሰው ተግበሩ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አመላክተዋል።
አክለውም ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተመረቁ ዜጎች የመንግስት ቅጥር ሳይጠብቁ እንዲሁም ሌሎች ወጣቶችም በየአካባቢው የሚገኙ ፀጋዎችን ተጠቅመው ሀብት እንዲያፈሩ ተቋሙ እያደረገ የሚገኘው ጥረት የሚያስመሰግነው እንደሆነ በመግለጽ የወጣቶቹ ተጠቃሚነት ይበልጥ እንዲጎለብት ከጨረታና ከኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ጀምሮ የገንዘብ ብድር የመስሪያና የመሸጫ ቦታዎች ቅድሚያ እንዲያገኙ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጀት የሚከናወኑ ተግባራት መጎልበት እንደሚገባቸውም አመላክተዋል ወ/ሮ ጠጄ።
በቋሚ የስራ እድል ፈጠራ ተግባር መዋቅሮችን ማቀራረብ ይገባል ያሉት የኢኮኖሚ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዋ፤ በተለይም ኢንተርፕራይዞች የገበያ ትስስር እንዲያገኙ ከወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ጋር በቅንጅት እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራትን አድንቀዋል።
ሁሉም መወቅሮች ለወጣቶች ተገቢውን በጀት መድበው ወደ ኦሞ ባንክ በማስገባት ለታለመለት አላማ ማዋል አለባቸው ያሉት ወይዘሮ ጠጄ፤ ብድር ካልተመለሰ ለወጣቱ ተጨማሪ የስራ እድል ለመፍጠር አደጋች ስለሚሆን በተዘዋዋሪ ፈንድ የተሰራጨው የገንዘብ ብድር ለማስመለስ እየተሰራ ያለው ንቅናቄ ማስቀጠል እንደሚገባም ጠቁመዋል።
የጉራጌ ዞን ስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙራድ ያሲን ተቋማቸው የ2018 1ኛ ግማሽ በጀት ዓመት ሪፖርት ለዞኑ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ አባላት አቅርቦ የአካል ግምገማ ከተደረገበት በዃላ ከአባላት በተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ላይ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ተቋማቸው ወጣቱ በዞኑ ውስጥ የሚገኙ ጸጋዎች በቅጡ ተመልክቶና ተረድቶ ወደ ተግባር በመግባት ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነቱ እንዲጎለብት እየሰራ ይገኛል ብለዋል አቶ ሙራድ።
ለማህበራት የተሰራጨው የገንዘብ ብድር አሟጦ በመሰብሰብ ለበርካታ ወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠር ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጀት እየተሰራ እንደሚገኝም አብራርተዋል።
ተቋማቸው በግማሽ በጀት አመቱ ለተለያዩ ማህበራት የገበያ ትስስር መፍጠሩን ያብራሩት አቶ ሙራድ በተለይም የወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ የተማሪዎች መቀመጫ ወንበር ማሰራቱን በማሳያነት ጠቅሰዋል።
ተቋማቸው አብዛኛዎቹ ከምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ አባላት የተነሱ ሃሳቦች በግብዓትነት ወስዶ ቀጣይ የተግባር አካል በማድረግ በውጤታማነት ለመፈፀም እንደሚሰራም አቶ ሙራድ አስረድተዋል።
ዘጋቢ፡ ሪድዋን ሰፋ – ከወልቂጤ ጣቢያችን

More Stories
በያዝነው ዓመት አስከ ጥቅምት ወር ድረስ 2 መቶ 50 ቶን በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ መላኩን የባስኬቶ ዞን ላስካ ዙሪያ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት አስታወቀ
የምርምር ተቋማት ከዝናብ ጥገኝነት ተላቀው የግብርናውን ስራ ውጤታማ እንዲያደርጉ የመስኖ ፕሮጀክት ግንባታ ስራ አስተዋጽኦው የጎላ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ኢንስቲትዩት አስታወቀ
የደረሱ ሰብሎችን በወቅቱ እና ያለብክነት ሊሰበሰብ እንደሚገባ የባኮ ዳውላ ኣሪ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት አሳሰበ