ሪያል ማድሪድ ኢብራሂማ ኮናቴን ማስፈረም አይፈልግም
የስፔኑ ክለብ ሪያል ማድሪድ የሊቨርፑሉን የመሀል ተከላካይ ኢብራሂማ ኮናቴን ማስፈረም እንደማይፈልግ ተገልጿል።
በያዝነው የውድድር ዓመት መጨረሻ በሊቨርፑል ቤት ያለው ኮንትራት የሚጠናቀቅበት ኢብራሂማ ኮናቴ በሪያል ማድሪድ በጥብቅ እንደሚፈለግ ሲነገር ቆይቷል።
እንደ ፋብሪዚዮ መረጃ መሰረት ሪያል ማድሪድ አሁን ላይ ግን ፈረንሳዊውን ተጫዋች የማስፈረም ፍላጎት እንደሌለው እና ከዝውውሩ ራሱን ማውጣቱን ለሊቨርፑል አሳውቋል።
የ26 ዓመቱ ተከላካይ ኢብራሂማ ኮናቴ እንደ አውሮፓውያኑ በ2021 በ36 ፓውንድ ከጀርመኑ ክለብ አርቢ ላይፕዚች ለመርሲሳይዱ ክለብ መፈረሙ ይታወሳል።
ዘጋቢ ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
ለልጁ የመሰለፍ ዕድልን የሰጠው ሌላኛው አሰልጣኝ
ማርቲን ኦዴጋርድ ወደ ልምምድ ተመለሰ
ወላይታ ድቻ በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ ድሉን አሳካ