ማርቲን ኦዴጋርድ ወደ ልምምድ ተመለሰ

ማርቲን ኦዴጋርድ ወደ ልምምድ ተመለሰ

የአርሰናሉ አምበል ማርቲን ኦዴጋርድ ከጉዳቱ በማገገም ወደ ልምምድ መመለሱ ተገልጿል።

ኖርዊያዊው የመሀል ስፍራ ተጫዋች በትከሻ ጉዳት ምክንያት ለሁለት ወራት ከሜዳ መራቁ ይታወሳል።

በነዚህ ግዚያት ውስጥም ሁለት የብሔራዊ ቡድኑ ጨዋታዎች እና 12 የአርሰናል ጨዋታዎች አልፈውታል።

አሁን ላይ ግን ኦዴጋርድ መድፈኞቹ በነገው ዕለት ከባየርንሙኒክ ጋር ከሚያደርጉት ወሳኝ የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ በፊት በአርሰናል የልምምድ ማዕከል ተገኝቶ ከቡድን አጋሮቹ ጋር በጋራ ልምምድ መስራቱ ተነግሯል።

ዘጋቢ ፡ ሙሉቀን ባሳ