ወላይታ ድቻ በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ ድሉን አሳካ
በ7ኛ ሳምንት የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ ወላይታ ድቻ ወልዋሎን 2 ለ 1 በማሸነፍ በዚህ የውድድር ዓመት የመጀመሪያ ድሉን አሳክቷል።
ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ለጦና ንቦች ወሳኝ የድል ጎሎችን ውብሸት ክፍሌ እና ቅዱስ ቂርቆስ አስገኝተዋል።
ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲን ከሽንፈት ያልታደገችውን ጎል ፍቃዱ መኮንን አስቆጥሯል።
ከ6 ጨዋታዎች በኋላ ከድል ጋር የተገናኘው ወላይታ ድቻ 5 ነጥቦችን በመያዝ ወደ 16ኛ ደረጃ ከፍ ብሏል።
በውድድር ዓመቱ 6ኛ የሊግ ሽንፈቱን ያስተናገደው ወልዋሎ በበኩሉ በ1 ነጥብ በደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ ላይ ይገኛል።
በሌላ የሊጉ መርሐግብር አዳማ ከተማ ባህር ዳር ከተማን በመርታት ወደ አሸናፊነት ተመልሷል።
በተመሳሳይ ሰዓት በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አቡበከር ሳኒ የአዳማ ከተማን የማሸነፊያ ጎል ከመረብ አሳርፏል።
ሊጉ በዚሁ በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም አመሻሽ ላይ መካሄዱን ሲቀጥል ኢትዮጵያ መድህን ከነገሌ አርሲ ጋር ከ12 ሰዓት ጀምሮ ይጫወታሉ።
ዘጋቢ ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
ማርቲን ኦዴጋርድ ወደ ልምምድ ተመለሰ
3ኛ የመቀስ ምት ጎሉ
ቼልሲ በርንሌይን በማሸነፍ ተከታታይ ድል አስመዘገበ