3ኛ የመቀስ ምት ጎሉ

ፖርቹጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በእግር ኳስ ተጫዋችነት ዘመኑ ለ3ኛ ጊዜ በመቀስ ምት ጎል አስቆጥሯል።

የ5 ጊዜ የባሎንዲኦር አሸናፊው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ትናንት ምሽት ክለቡ አልናስር በሳውዲ ፕሮ ሊግ 9ኛ ሳምንት መርሐግብር አል ካሌጅን 4ለ1 በረታበት ጨዋታ በመቀስ ምት ግሩም ኳስ ከመረብ አሳርፏል።

የ40 ዓመቱ ተጫዋች በእግር ኳስ ተጫዋችነት ህይወቱ ያስቆጠራቸውን ጎሎች 954 አድርሷል።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ የመጀመሪያ የመቀስ ምት ጎሉን ያስቆጠረው በፈረንጆቹ 2018 ላይ ሪያል ማድሪድ ጁቬንቱስን 3ለ0 በረታበት ጨዋታ ነው።

2ኛ የመቀስ ምት ጎሉን ደግሞ በ2024 ፖርቹጋል ፖላንድን 5ለ1 ስትረታ አስቆጥሯል።

ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ