ሀዋሳ ከተማ መቀሌ 70 እንደርታን አሸነፈ
በ4ኛ ሳምንት የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሀዋሳ ከተማ መቀሌ 70 እንደርታን በማሸነፍ ተከታታይ አስመዝግቧል።
ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሀዋሳ ከተማ መቀሌ 7ዐ እንደርታን 3ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
ለሀዋሳ ከተማ የድል ግቦችን ጌታነህ ከበደ ሁለት ጎሎችን ሲያስቆጥር ያሬድ ብሩክ ደግሞ ቀሪዋን ግብ ከመረብ አሳርፏል።
መቀሌ 70 እንደርታን ከሽንፈት ያልታደገችውን ጎል ሱሌማን ሀሚድ አስቆጥሯል።
በጨዋታው የሀዋሳ ከተማው ተከላካይ በረከት ሳሙኤል በሰራው ጥፋት በሁለት ቢጫ ቀይ ካርድ ተመልክቶ ከሜዳ ወጥቷል።
ጌታነህ ከበደ ለሀዋሳ ከተማ በፕሪሚዬር ሊጉ 3ኛ ጎሉን ነው ያስቆጠረው።
በዚህ ዓመት 3ኛ ድሉን ያስመዘገበው ሀዋሳ ከተማ ነጥቡን 9 በማድረስ 4ኛ ደረጃን ይዟል።
ዘጋቢ ፡ሙሉቀን ባሳ

                
                                        
                                        
                                        
                                        
More Stories
ኦክስሌድ ቻምበርሌን በአርሰናል ልምምድ መስራት ጀመረ
ቱርክ 149 የእግር ኳስ ዳኞችን አገደች
ፓትሪክ ቬራ ከጄኖኣ ሀላፊነት ተሰናበተ