ሞርጋን ሮጀርስ በአስቶንቫላ ለመቆየት ውሉን አራዘመ
እንግሊዛዊው የፊት መስመር ተጫዋች ሞርጋን ሮጀርስ በአስቶንቫላ ለተጨማሪ ዓመታት ለመቆየት ውሉን አራዝሟል።
የ23 ዓመቱ ተጫዋች በቪላ ፓርክ እንደ አውሮፓውያኑ እስከ 2031 ድረስ የሚያቆየውን አዲስ ኮንትራት መፈረሙን ክለቡ አሳውቋል።
ተጫዋቹ በአዲሱ ውል የደሞዝ ጭማሪ እንደተደረገለት ተገልጿል።
ሞርጋን ሮጀርስ በ2024 በጥር የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ከሚድልስቦሮው ለአስቶንቪላ መፈረሙ ይታወሳል።
ክለቡን በቶሎ በመላመድ አስደናቂ እንቅስቃሴን ማሳየት የቻለው ሮጀርስ ለበርሚንግሃሙ ክለብ እስካሁን 86 ጨዋታዎችን በማከናወን 18 ጎሎችን ሲያስቆጥር 20 ግብ የሆኑ የመጨረሻ ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል።
ዘጋቢ፡ሙሉቀን ባሳ

More Stories
አንጎል ሦስት የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾችን ከለከለች
ሀዋሳ ከተማ መቀሌ 70 እንደርታን አሸነፈ
ኦክስሌድ ቻምበርሌን በአርሰናል ልምምድ መስራት ጀመረ