ሀገሪቱን ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በማሸጋገር በማህበራዊም ሆነ በኢኮኖሚ ዘርፍ ተጠቃሚ ለማደረግ ሁሉም አካላት የበኩላቸውን ድርሻ ሊወጡ እንደሚገባ የይርጋጨፌ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ

ሀገሪቱን ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በማሸጋገር በማህበራዊም ሆነ በኢኮኖሚ ዘርፍ ተጠቃሚ ለማደረግ ሁሉም አካላት የበኩላቸውን ድርሻ ሊወጡ እንደሚገባ የይርጋጨፌ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ

ጽ/ቤቱ “ከተረጅነት ወደ ምርታማነት” በሚል መሪ ቃል የ2017 አፈፃፀምና የ2018 ዕቅድ ዙሪያ የምክክር መድረክ እያካሄደ ይገኛል።

መድረኩ ባለፉት ጊዜያት የነበሩ ስኬቶችንና ችግሮችን በመለየት ለቀጣይ ውይይት በማድረግ ለጋራ ችግሮች በጋራ መፍትሔ መፈለግ ላይ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

በውይይቱ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የይርጋጨፌ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ክፍሌ ጅክሶ፣ በሀገራችን ስር ሰዶ የቆየውን የተረጂነትና የልመና አስተሳሰብ ለማስወገድ ህዝቡን ወደ ላቀ ምርታማነት ደረጃ ማሸጋገርና በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እየተሠራ መቆየቱን ተናግረዋል።

በቀጣይም ሀገሪቱን ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በማሸጋገር በማህበራዊም ሆነ በኢኮኖሚ ዘርፍ ተጠቃሚ ለማደረግ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መሥራት እንደሚገባ ኃላፊው አስገንዝበዋል።

በመድረኩ ላይ የወረዳውን አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ቡኔን ጨምሮ የወረዳው የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች፣ የተለያዩ አደረጃጀቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እየተሳተፉ ነው።

ዘጋቢ፡ ዘርሁን ሹፌር – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን