የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት እና የብሔረሰቦች ምክር ቤት የዞን፣ የረጂዮ ፖሊስ ከተማ ምክር ቤት የጋራ ምክር ቤቶች የ2018 በጀት ዓመት 3ኛ ዙር የጋራ ምክክር ፎረም እየተካሄደ ነው

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት እና የብሔረሰቦች ምክር ቤት የዞን፣ የረጂዮ ፖሊስ ከተማ ምክር ቤት የጋራ ምክር ቤቶች የ2018 በጀት ዓመት 3ኛ ዙር የጋራ ምክክር ፎረም እየተካሄደ ነው

ምክር ቤቶች የራሳቸውን ተግባር ከሚገመግምበት መንገድ የጋራ ምክክር ፎረም አንዱ ነው ብለው፤ እንግዶችን በእንኳን ደህና መጣችሁ የተቀበሉት የኣሪ ዞን ሽግግር ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ስመኝ ተስፋዬ ናቸው።

ምክር ቤቶች በተናጠል ከሚሠሩት በተጨማሪ በጋራ መወያየት ዴሞክራሲን ይበልጥ ማጎልበት እንደሆነ የገለፁት የኣሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም አታ፤ በየአካባቢው የተከናወኑ ሥራዎችን ምልከታ በማድረግ ይበልጥ የሕዝቡ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ያደርጋል ብለዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ አለማየሁ ባውዲ፤ ኢትዮጵያ ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ ከለውጡ ማግስት የተለያዩ አስደማሚ ስኬቶችን እያስመዘገበች ትገኛለች ብለዋል።

ዴሞክራሲያዊ ልምምዶችን በማጠናከር ፍትሐዊ ሀገራዊ ምርጫ ለማድረግ ዝግጅት የሚደረግበት ጊዜ ላይ እንገኛለን ሲሉም አቶ አለማየሁ ገልፀዋል።

ድህነትን ለማስቀረት በጊዜ የለሽ እና በሀላፊነት መንፈስ መሥራት ይጠበቅብናል ሲሉም ከቶ አለማየሁ በዚሁ ወቅት አንስተዋል።

የፎረሙ መድረክ ዋና ዋና የሁለቱ ምክር ቤቶች ተግባራትን በመለየት ለተሻለ አፈፃፀም መግባባት ላይ የሚደረስበት እንደሆነም አፈ ጉባኤው አስረድተዋል።

በመድረኩ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሁለቱ ምክር ቤቶች ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሀላፊዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም ከክልሉ ሥር ካሉ መዋቅሮች ተገኝተዋል።

በመድረኩ የተለያዩ የሥራ ሐሳቦችን የያዙ ሰነዶች ቀርበው በጥልቀት ውይይት በማድረግ የጋራ ስምምነት እንደሚደረግ ይጠበቃል።

ዘጋቢ: ተመስገን አበራ – ከጂንካ ጣቢያችን