የ2018 የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ይጀመራል

ከባለፉት 5 ዓመታት በተለየ የውድድር ቅርፅ በሁለት ምድቦች ተከፍሎ የሚካሄደው የዚህ ውድድር ዓመት የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በዛሬው ዕለት ሀዋሳ እና አዲስ አበባ ላይ ጅማሮውን ያደርጋል።

በፕሪሚየር ሊጉ የመክፈቻ ጨዋታ በሁለት ስታዲየሞች በድምሩ አራት ፍልሚያዎች የሚከናወኑ ይሆናል።

በዚህም መሰረት በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ከሲዳማ ቡና ጋር ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ።

አመሻሽ 12 ሰዓት ላይ ደግሞ ድሬዳዋ ከተማ ከሀዋሳ ከተማ የሚጫወቱ ይሆናል።

ከስድስት ዓመታት በኋላ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን ለማስተናገድ በተዘጋጀው የአዲስ አበባ ስታዲየም ላይ የዘንድሮው የውድድር ዓመት የመክፈቻ መርሐግብር ኢትዮ ኤሌክትሪክን ከሸገር ከተማ ጋር ይገናኛል።

ጨዋታው ከቀኑ 7 ሰዓት ላይ ይካሄዳል።

10 ሰዓት ላይ ደግሞ አርሲ ነገሌ ከአርባምንጭ ከተማ ጋር ይጫወታሉ።

ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ