ሊድያ ታፈሰ የካፍ የዳኞች ኮሚቴ አባል ሆና ተመረጠች

ሊድያ ታፈሰ የካፍ የዳኞች ኮሚቴ አባል ሆና ተመረጠች

ሀዋሳ፡ ጥቅምት 07/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) የቀድሞ ዓለም አቀፍ ዳኛ ሊዲያ ታፈሰ የካፍ የዳኞች ኮሚቴ አባል ሆና ተመርጣለች።

የብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ በመሆን እያገለገለች የምትገኘው ሊዲያ ታፈሰ ካፍ በአዲስ መልክ ባዋቀረውና 12 አባላት ባሉት ኮሚቴ አባል ሆና መመረጧን ከኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የተገኘው መረጃ ያስረዳል።

ሊዲያ ታፈሰ የዳኞች ኢንስትራክተር መሆኗ ይታወቃል።

ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ