ቼልሲ ኖቲንግሃም ፎረስትን በማሸነፍ ደረጃውን አሻሻለ
በ8ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ቼልሲ ከሜዳው ውጪ ኖቲንግሃም ፎረስትን 3ለ0 በማሸነፍ ደረጃውን አሻሽሏል።
በሲቲ ግራውንድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ለምዕራብ ለንደኑ ክለብ የድል ግቦችን ጆሽ አቼንፖንግ፣ ፔድሮ ኔቶ እና ሪስ ጄምስ በሁለተኛው አጋማሽ አስገኝተዋል።
በጨዋታው በቼልሲ በኩል ማሎ ጉስቶ በሁለት ቢጫ ቀይ ካርድ ተመልክቶ ከሜዳ ወጥቷል።
እንግሊዛዊው የመሀል ተከላካይ ጆሽ አቼንፖንግ ለቼልሲ የመጀመሪያ ጎሉን ነው ያስቆጠረው።
አሰልጣኝ አንጄ ፖስቴኮግሉ በኖቲንሃም ፎረስት ቤት 8 ተከታታይ ጨዋታዎችን ማሸነፍ ሳይችሉ ቀርተዋል።
አውስትራሊያዊው አሰልጣኝ ከቼልሲ ጋር በተገናኙባቸው አምስቱም ጨዋታዎች ሽንፈት አስተናግደዋል።
ቼልሲ ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን 14 በማድረስ በጊዚያዊነት 4ኛ ደረጃን መያዝ ሲችል ኖቲንግሃም ፎረስት በበኩሉ በ5 ነጥብ 17ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
የሊጉ መርሐግብሮች መካሄዳቸውን ሲቀጥሉ ማንቸስተር ሲቲ በሜዳው ከኤቨርተን ጋር 11 ሰዓት ላይ የሚያደረገው ጨዋታ ተጠባቂ ነው።
በተመሳሳይ ሰዓት ሰንደርላንድ ከዎልቭስ፣ ክርስታል ፓላስ ከበርንማውዝ፣ በርንሌይ ከሊድስ ዩናይትድ እንዲሁም ብራይተን ከኒውካስል ዩናይትድ ይጫወታሉ።
ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ላይ ደግሞ የሊጉ መሪ አርሰናል ከሜዳው ውጪ ከፉልሃም ጋር ይፋለማል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ
More Stories
ማንቸስተር ሲቲ ኤቨርተንን በማሸነፍ የሊጉ መሪ ሆነ
ኖቲንግሃም ፎረስት አንጅ ፖስቴኮግሉን አሰናበተ
ሲዳማ ቡና የውድድር ዓመቱን በድል ጀመረ