‎አርሶአደሩ አረምና ተባይን በመቆጣጠር ምርትና ምርታማነትን እንዲያሳድግ እየተሠራ መሆኑን የኮሬ ዞን ግብርና መምሪያ አስታወቀ

‎አርሶአደሩ አረምና ተባይን በመቆጣጠር ምርትና ምርታማነትን እንዲያሳድግ እየተሠራ መሆኑን የኮሬ ዞን ግብርና መምሪያ አስታወቀ

‎በ2018 መኸር እርሻ ከ1 ሚሊዮን 50 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት እንደሚጠበቅም የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታውቋል።

‎በኮሬ ዞን ግብርና መምሪያ የሰብል ልማትና ጥበቃ ቡድን መሪ አቶ አሸናፊ አሳምነው፤ በዘንድሮው የመኸር እርሻ ከ70 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት በተለያዩ የሰብል ዓይነቶች መሸፈኑን ገልጸው በአብዛኛው ከአንድ ጊዜ በላይ የአረም ተግባር መከናወኑን ተናግረዋል።

‎በአጠቃላይ በዞን ደረጃ የመኸር እርሻ ከዕቅድ በላይ መሸፈኑን የገለጹት ቡድን መሪው 1 ሚሊዮን 54 ሺህ ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅ ገልጸዋል።

‎በዞኑ ጎርካ ወረዳ በዝናብ እጥረት የአረም ቁጥጥር መጓተቱን ያነሱት አቶ አሸናፊ፤ በአሁኑ ወቅት ባለው እርጥበት አርሶአደሩ አረምና ተባይን በመቆጣጠር ምርትና ምርታማነትን እንዲያሳድግ አሳስበዋል።

‎ከዞቀሳና ጋሙሌ ቀበሌ ያነጋገርናቸው አርሶአደር ገላዬ ጩሉሲ እና ዘለሉ አየለ ለረዥም ሳምንታት ተቋርጦ የነበረው ዝናብ በመጀመሩ በእጅ በማረምም ሆነ ፀረ አረም በመርጨት አረምን የመቆጣጠር ተግባር ላይ መሆናቸውን ነው የተናገሩት።
‌‎
‎ዘጋቢ፡ ምርጫ መላኩ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን