ህዝብ ያነሳቸው የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት በቅንጅት የተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤት ማምጣታቸው ተገለጸ
ሀዋሳ፡ መስከረም 27/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) ህዝብ ያነሳቸው የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት በቅንጅት የተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤት ማምጣታቸውን የጉራጌ ዞን ምክር ቤት አስታወቀ።
የዞኑ ምክር ቤት የ10 ወረዳዎች እና የ5 ከተማ ምክር ቤቶች 4ኛ ዙር 13ኛ ዓመት 25ኛ የአፈ- ጉባኤዎች የጋራ ምክክር መድረክ በወልቂጤ ከተማ አካሂዷል።
የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ዋና ጉባኤ አቶ ኸይሩ መሐመድ በጉባኤው ላይ እንዳሉት በ2017 በጀት ዓመት በየመዋቅሩ የሚገኘው የዞኑ ህዝብ ያነሳቸው የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ምላሽ ለመስጠት በቅንጅት የተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤት አስገኝተዋል።
ውጤቱ እንዲመዘገብ የዞኑ ምክር ቤት የህዝብ አይን እና ጆሮ ሆኖ በርካታ ተግባራት መፈጸሙን ያነሱት ዋና አፈ-ጉባኤው ተግባሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ጠቁመዋል።
በየደረጃው የሚገኙ ምክር ቤቶች ድጋፍና ክትትል በማድረግ እና የአሰራር ክፍተቶችን በመለየት ሙያዊ ድጋፍ በማድረግ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎችን ተሰጥቷል ብለዋል።
ምክር ቤቱ በድጋፍና ክትትል ወቅት የተገኙ ምርጥ ተሞክሮዎችን በመለየትና በመቀመር ወደ ሌሎች በማስፋት ምክር ቤቶች ተግተው በመስራት ሚናቸውን እንዲያሳድጉ ከፍተኛ እገዛ ሲያደርግ መቆየቱን ተናግረዋል።
በበጀት አመቱ የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማሻሻል ተገቢውን ክትትልና ቁጥጥር ተደርጎ ጥራት ያለው ምዘና በማካሄድ ጠንካራ አፈጻጸሞች በተሞክሮነት እንዲቀመሩ በአንጻሩ ደግሞ ክፍተቶችን እንዲሞሉ ጠንካራ ግብረ መልስ መሰጠቱንም ዋና አፈጉባኤው አቶ ኸይሩ አመላክተዋል።
በጉራጌ ዞን ምክር ቤት የማህበራዊ ዘርፍ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ጥሩነሽ ምኑታ በበኩላቸው በ2017 በጀት አመት የተሰሩ ስራዎች አበረታች ውጤቶች የታዩባቸው እንደነበሩ ጠቅሰው ይህም በሪፖርት፣ በገፅ ለገፅ እና በመስክ ምልከታ ወቅት ማረጋገጥ መቻሉንም ተናግረዋል።
የተከናወኑ ተግባራት ይበል የሚያሰኙ በመሆናቸው የህዝብ ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ የትብብር ስራዎች አጠናክሮ ማስቀጠልን ይጠይቃል ብለዋል።
በመድረኩ ያነጋገርናቸው የምክር ቤት አባላት በሰጡት አሰተያየት በየደረጃዉ ህዝቡ የሚያነሳቸው የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ የተደረገው ርብርብ ተስፋ ሰጪ በመሆኑ አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ነው ያሉት።
በምክር ቤቶች የሚሰሩ ስራዎች ክብደትና ትርጉም ተሰጥቷቸዉ ጠንካራ አፈፃፀሞች ለማስፋትና የነበሩ ጉድለቶች ለማረም እንዲሁም የመዋቅሮች አፈፃፀም ለማቀራረብ የሚከናወኑ ተግባራት ይበልጥ እንዲጎለብቱ ተባብረው በመስራት ላይ እንደሚገኙም አስተያየት ሰጪዎቹ ተናግረዋል።
የፎረም እቅድ የሚያሰራና የቀበሌ ምክር ቤቶች የሚያጠናክር እንደሆነም አመላክተዋል።
በፎረሙ በ2018 ጠቋሚ እቅድ ላይ ከመምከር ባለፈ በባለፈው አመት የተግባር አፈጻጸም ወቅት የነበሩ የተሻሉ አፈጻጸሞችን ለማጠናከርና ጉድለቶችን ለማረም ውይይት በማድረግ የቀጣይ አቅጣጫ ተቀምጧል።
በመድረኩ በ2017 በጀት አመቱ የተሻለ አጸፃፀም ላስመዘገቡ ተቋማት እና ግለሰቦች እውቅና እና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል ።
ዘጋቢ፡ ሪድዋን ሰፋ – ከወልቂጤ ጣቢያችን
More Stories
ምግብና ሥርዓተ-ምግብን በማሻሻል የቤተሰብ ብልጽግናን ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ ገለጸ
የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በምርምር የተረጋገጡ አዳዲስና የተሻሻሉ ቴክኖሎጂዎችን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ
የቀይ አፈር ሙሉ ወንጌል ነህምያ የልጆች ልማት ከደቡብ ኦሞ ዞን ሴቶችና ሕፃናት መምሪያ ጋር በመተባበር “የዎና ናና” የህፃናት ልማት ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ በዲመካ ከተማ ተካሂዷል