በሩብ አመቱ 1ሺህ 600 ሄ/ር መሬት ለአልሚ ባለሀብቶች መተላለፍ መቻሉ ተገለጸ
ሀዋሳ፡ መስከረም 27/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) በተጠናቀቀው ሩብ ዓመት 1ሺህ 600 ሄ/ር መሬት ለአልሚ ባለሀብቶች ማስተላለፍ መቻሉን የቤንች ሸኮ ዞን ንግድና ኢንቨስትመንት መምሪያ ገለፅ።
የቤንች ሸኮ ዞን ንግድና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ አቶ ኮጅ ባዳካች እንደገለፁት ዞኑ ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ፍሰት ያለበት እንደሆነ ጠቁመው፥ በበጀት ዓመቱ በአገልግሎት፣ በግብርናና በኢንዱስትሪ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል ብለዋል ።
በተጠናቀቀው ሩብ ዓመት 2ሺ ሄ/ር መሬት ለመለየት ታቅዶ 3ሺ 761 ሄ/ር የመለየት ስራ መሰራቱን አቶ ኮጅ ተናግረዋል ።
በዚህም በ2017 ተለይቶ ባለቤት ለተፈጠረላቸው አልሚዎች መሬት ማስረከብ ብቻ ሳይሆን ወደ ስራ ገብተው ማልማት እንዲችሉ በርካታ ስራዎች መሰራቱን አመላክተዋል።
የተለዩ መሬቶችን እንዲያለሙ በግብርና 8፣ በኢንድስትሪ 5፣ በአገልግሎት 6 በአጠቃላይ 19 ፕሮጆክቶች ላይ ፍቃድ የመስጠት ስራ ከማከናወን ባለፈ 5 ነባር ኢንቨስትመንቶች ፍቃድ እንዲያድሱ ታቅዶ ሁለት ኢንቨስትመንት እድሳት ማድረጋቸውን አቶ ኮጅ ባዳካች ተናግረዋል።
በዘርፉ የተሳተፉ ከ108 ሚሊዬን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሀብቶች ሲሆኑ እነዚህም በ8 ኢንበስትመንት በዚህ ሩብ ዓመት 1ሺ 600ሄ/ር መሬት ማስረከብ መቻሉን የመምሪያው ሃላፊ ተናግረዋል ።
ኢንቨስትመንት ለሀገር ኢኮኖሚ የሚያበረክተው አስተዋፆ ከፍተኛ ነው ያሉት አቶ ኮጅ በዞኑ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለ ገልፀው ይህንን ሁሉም መዋቅር የመሬት አቅማቸውን ለይተው ጥናት በማድረግ ዘርፉን ማበልፀግ ይገባል ብለዋል ።
ዞኑ ሰፊ የሆነ ለሆቴል ቱሪዝም፣ የግብርናና የማዕድን፣ ፀጋዎችን የታደለ በመሆኑ ባለሀብቶች ወደ አካባቢው መጥተው እንዲያለሙ ጥሪ አቅርበዋል።
ዘጋቢ፡ ዮናስ ወ/ገብሬኤል – ከሚዛን ጣቢያችን
More Stories
ምግብና ሥርዓተ-ምግብን በማሻሻል የቤተሰብ ብልጽግናን ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ ገለጸ
የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በምርምር የተረጋገጡ አዳዲስና የተሻሻሉ ቴክኖሎጂዎችን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ
የቀይ አፈር ሙሉ ወንጌል ነህምያ የልጆች ልማት ከደቡብ ኦሞ ዞን ሴቶችና ሕፃናት መምሪያ ጋር በመተባበር “የዎና ናና” የህፃናት ልማት ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ በዲመካ ከተማ ተካሂዷል