በክረምት ወራት የታየውን ትጋት በበጋውም ለመድገም ቁርጠኞች መሆናቸውን በጌዴኦ ዞን የይርጋጨፌ ከተማ ወጣቶች ተናገሩ
በከተማው የ2017 ዓ.ም የክረምት ወራት የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማጠቃለያ እና የ2018 ዓ.ም የበጋውን ማስጀመሪያ መርሃግብር ተካሂዷል።
በከተማው በአምናው የክረምት ወራት የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት የተከናወኑ ተግባራት የበርካታ ወገኖችን እንባ ያበሰ እንደነበረ ነው የተገለጸው።
በወጣቶቹ አገልግሎት 3 መቶ 42 የሚሆኑ የአቅመ ደካሞች ቤቶች ግንባታና እድሳት አንደተከናወነ የተገለፀ ሲሆን በከተማ ጽዳት ዘርፈ ብዙ ተግባራት ተከናዉነዋል ተብሏል።
ከ18 ሺህ በላይ የሚሆኑ ወጣቶች በተሰማሩበት በዚህ በጎ ተግባር ከ79 ሺህ በላይ የሚሆኑ ወገኖች ተጠቃሚ መሆናቸውንና አገልግሎቱ በገንዘብ ሲተመን ከ29 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚሆንም ተገልጿል።
በእነዚህ በጎ ተግባራት ከተሰማሩ ወጣቶች መካከል ወጣት አማከለች አየለ፣ ይታገሱ ወርቁ እና ሌሎችም በሰጡት አስተያየት በክረምት ወራት በነበረው አገልግሎት በተለያዩ ተጽዕኖዎች ሳይገደቡ በትጋት ሲሠሩ መቆየታቸውን ጠቅሰው በበጋዉም ለመድገም ቁርጠኞች መሆናቸውን አስረድተዋል።
በከተማው አስተዳደር የወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ባህሩ ማሞ በበኩላቸው ባለፈው ዓመት የተመዘገበው የቅንጅት ውጤት እንደሆነ ገልጸው በበጋውም ለመድገም እየሠሩ እንደሚገኙም አስገንዝበዋል።
ዘጋቢ፡ አማኑኤል ትዕግሥቱ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን

More Stories
7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ምክንያት በማድረግ የብልጽግና ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች የምረጡን ቅስቀሳና ድጋፍ ሰልፍ በኣሪ ዞን ጋዘር ከተማ አካሄዱ
በጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳ እና በላሃ ከተማ አስተዳደር የብልጽግና ፓርቲ የማጠቃለያ ሕዝባዊ የምርጫ ቅስቀሳ ፕሮግራም ተካሄደ
የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምጽ መስጫ ቀን 7 ቀናት ብቻ ቀርተውታል