ፕሮጀክቱን እውን ለማድረግ በቁርጠኝነት እየሠሩ መሆናቸውን በደቡብ ኦሞ ዞን የዎባ አሪ ወረዳ አርሶ አደሮች ገለፁ
ሀዋሳ፡ ሰኔ 15/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) 30 40 30 የፍራፍሬ ልማት ፕሮጀክትን እውን ለማድረግ በቁርጠኝነት እየሠሩ መሆናቸውን በደቡብ ኦሞ ዞን የዎባ አሪ ወረዳ አርሶ አደሮች ገልፀዋል፡፡
የወረዳውን የተፈጥሮ ፀጋዎችን ለፍራፍሬና ቅባት እህሎች በመጠቀም የአርሶ አደሩ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የወረዳው አስተዳደር እንደሚሠራ አስታውቋል፡፡
በደቡብ ኦሞ ዞን ዎባ አሪ ወረዳ የ30 40 30 የፍራፍሬ ልማት ፕሮጀክት ሁለተኛ ዓመት የማስጀመሪያ መርሃ-ግብር የወረዳው አመራሮችና ባለድርሻ አካላት በተገኙት ተከናውኗል፡፡
በችግኝ ተከላው የተገኙ አርሶ አደሮች እንደተናገሩት፤ ፍራፍሬዎች ለኑሮአችን ዋስትና ስለሆኑ የተተከለው ችግኝ ፀድቆ ፍሬ እስኪያፈራ እንክብካቤ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል፡፡
በወረዳው ለግብርና ዕድገት ማነቆ የሆኑ ችግሮችን በመቅረፍ የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እየሠሩ መሆናቸውን የገለፁት የግብርና እድገት ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ቢሻው መካሪ ናቸው፡፡
የዎባ አሪ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሽብሩ ተካልኝ እንደተናገሩት፤ ለማህበረሰቡ በአጭር ጊዜ የሚደርሱ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው የፍራፍሬ ችግኝ ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን ማቅረባቸውን ገልፀው አምና የተተከሉ የፍራፍሬ ችግኞች 89 በመቶ መፅደቃቸውን አስረድተዋል፡፡
የወረዳውን የተፈጥሮ ፀጋዎችን በመጠቀም የአርሶ አደሩ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሠራ የገለፁት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኢያሱ ዘርፉ ህዝቡ ለፍራፍሬ ልማት ትኩረት እንዲሰጥ አሳስበዋል፡፡
ዘጋቢ: ተመስገን አሰፋ – ከጂንካ ጣቢያችን

More Stories
የሀለባ ዞን ምክር ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ከ3 ቢልዮን 293 ሚልዮን ብር ባለይ በጀት አጸደቀ
መስራት እየቻሉ የገንዘብ እጥረት የገጠማቸው የህብረተሰብ ክፍሎችን ችግሮች ለመፍታት የህብረት ስራ ማህበራት ሚና ቀላል አለመሆኑ ተገለጸ
በስልጤ ልማት ማህበር ለ3ኛ ጊዜ በተዘጋጀው የችግኝ ተከላ መርሀግብር ከሀገር ውስጥና ከውጪ ሀገር የተሰበሰቡ የአካባቢው ተወላጆች በዞኑ በሚገኙ የላንፉሮ ወረዳና ጦራ ከተማ አስተዳደር ችግኞችን ተክለዋል ።