”ያሆዴ” የአንድነት፣ የፍቅርና መተሰሳሰብ በዓል በደማቅ ስነስርዓት እየተከበረ ነው
”ያሆዴ” አንድነት፣ ፍቅርና መተሰሳሰብ ጎልቶ የሚወጣበት የተነፋፈቁ ወገኖች የሚገናኙበት፣ እርቅ የሚወርድበት፣ ከመገፋፋት ይልቅ መቀራረብ የሚመረጥበት፣ ከጨለማ ወደ ብርሃን መውጣት የሚታወጅበት የአብሮነት ተምሳሌት ነው።
የሀዲያ ብሔር ዘመን መለወጫ የያሆዴ በዓል በሆሳዕና ከተማ በሀዲይ ነፈራ በደማቅ ስነ-ስርዓት እየተከበረ ይገኛል ።
በበዓሉ ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርእሰ መስተዳድር እንዳሸው ጣሰው(ዶ/ር)፣ የኤፌዴሪ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሬ፣ የሀድያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማቲዎስ አኒዮ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ የዞን፣ የወረዳዎችና የከተማ አስተዳደሮች የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ፣የባህል ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ ከሀገር ዉጪ እና ከተለያዩ አካባቢዎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳታፊዎች ሆናዋል።
ዘጋቢ: በየነ ሰላሙ – ከሆሳዕና ጣቢያችን
More Stories
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ስራና ክህሎት ቢሮ “ብቃት ለቴክኒክና ሙያ ልህቀት!” በሚል መሪ ቃል በቦንጋ ክላስተር ለሚገኙ የቴክኒክና ሙያ አሠልጣኞች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና መስጠት ጀምሯል