የጤና ፕሮግራምና ኤች አይ ቪ መከላከልና መቆጣጠር ዘርፍ የተግባር አፈፃፀም ግምገማና የውይይት መድረክ ተካሄደ
ሀዋሳ፡ የካቲት 26/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የ2018 ዓ/ም የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የጤና ፕሮግራምና ኤች አይ ቪ መከላከልና መቆጣጠር ዘርፍ የተግባር አፈፃፀም ግምገማና የውይይት መድረክ በጂንካ ከተማ አካሂዷል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የጤና ፕሮግራምና ኤች አይ ቪ መከላከልና መቆጣጠር ዘርፍ ኃላፊ አቶ መና መኩሪያ እንደገለፁት፥ በቢሮ ሥር ያሉ የዘርፍ የሥራ ክፍሎች በተናበበና በተቀናጀ መልኩ ሥራ ቆጥረው ውጤት እንዲያስመዘግቡ እየተሠራ መሆኑ ተመላክቷል።
በክልሉ ያሉ መዋቅሮች በዚህ ልክ እንዲተገብሩ ድጋፍና ክትትል እየተደረገ ሲሆን፥ የመድረኩ ተሳታፊዎች የቀረቡ የ2018 ዓ/ም የመጀመሪያ ስድስት ወራት የዘርፉ አፈፃፀሞች ላይ ክፍቶችን ለማረም እንዲሠሩ አቶ መና አሳስበዋል።
የወባ ወረርሽኝ በተለያየ ጊዜ በክልሉ ስር የሚስተዋልበት ሁኔታ ስለመኖሩና ቢሮ ይህንን በመቆጣጠር ሂደት በሰጠው ልዩ ትኩረት ውጤት መመዝገቡን አቶ መና መኩሪያ ጠቅሰው፥ ሆኖም አሁንም በወባ በሽታ ዙሪያ ብዙ ሥራን ይጠይቃል ብለዋል።
በሁሉም የጤና አገልግሎት ዘርፎች አሁን ያለው አፈፃፀም ዓመቱ ሲጠቃለል በሚፈለገው ልክ ውጤት እንዲመዘገብ የመድረኩ ተሳታፊዎች በቁርጠኝነት ሊሠሩ ይገባል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የመድረኩ ተሳታፊዎች ከቀረበው የየዘርፉ የጤና አገልግሎቶች በምን ደረጃ ላይ እንዳሉ የሚያሳይ መረጃ ማግኘታቸውን ጠቅሰው፥ ወደ መጡበት አካባቢ ሲመለሱ ያለባቸውን ክፍተት ለማረምና ለህዝቡ ተጠቃሚነት እንደሚሠሩ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
ዘጋቢ: ተመስገን አበራ – ከጂንካ ጣቢያችን

More Stories
የህዝቡ የልማትና የመልካም አስተዳዳር ጥያቄዎች በዘላቂነት እንዲመለሱ ከየትኛውም ጊዜ በላይ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኧሌ ዞን ሽግግር ምክር ቤት ገለፀ
መንግስት የደን ጭፍጨፋን በመከላከል የአየር ሚዛንን ለመጠበቅ በሚያደርገው ጥረት ውስጥ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ደን፣ አካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ ቢሮ እስታውቀ
የህዝቡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመቅረፍ እንዲያስችል ዞኑ የሚያመነጨውን ገቢ በአግባቡ መሰብሰብ እንደሚገባ የጉራጌ ዞን አስተዳደር አስታወቀ