የ5000 ሜትር ሴቶች የፍፃሜ ውድድር ዛሬ ይካሄዳል
በጃፓን ቶኪዮ እየተካሄደ ባለው 20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች የሚካፈሉበት የሴቶች 5 ሺህ ሜትር የፍፃሜ ውድድር ከቀኑ 9 ሰዓት ከ29 ደቂቃ ጀምሮ ይካሄዳል።
ኢትዮጵያ በርቀቱ በ3 እንስት አትሌቶች ትወከላለች።
አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ፣ መዲና ኢሳ እና ፋንታዬ በላይነህ ለኢትዮጵያ ሜዳልያ ለማስገኘት የሚፋለሙ አትሌቶች ናቸው።
ኢትዮጵያ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ5 ሺህ ሜትር ሴቶች እስከአሁን 6 የወርቅ፣ 3 የብር እና 8 የነሃስ ሜዳልያዎችን በማሸነፍ ስኬታማ ሆና ትገኛለች።
ዛሬ በሚካሄደው የ5 ሺህ ሜትር ፍፃሜ ውድድር ላይ በርቀቱ በውድድሩ ታሪክ ፈጣን ሰዓት ያስመዘገቡ አራት አትሌቶች ለፍፃሜ ደርሰዋል።
አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ፣ ሦስቱ ኬንያዊያን አትሌቶች ቢአትሪስ ቼቤት፣ ፌይዝ ኪፕዬጎን እና አግኔስ ንጌቲች በርቀቱ ፈጣን ሰዓት ያላቸው አትሌቶች ናቸው።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
ማርቲን ኦዴጋርድ ወደ ልምምድ ተመለሰ
ወላይታ ድቻ በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ ድሉን አሳካ
3ኛ የመቀስ ምት ጎሉ