ዊሊያም ሳሊባ በአርሰናል ውሉን ለማራዘም ተስማማ

ዊሊያም ሳሊባ በአርሰናል ውሉን ለማራዘም ተስማማ

ሀዋሳ፡ መስከረም 15/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) ፈረንሳዊው የመሐል ስፍራ ተከላካይ በአርሰናል ውሉን ለተጨማሪ ዓመት ለማራዘም ከስምምነት ላይ መድረሱ ተገለጸ።

የ24 ዓመቱ ተጫዋች በመድፈኞቹ ቤት የረዥም ዓመት ውል ለመፋራረም መስማማቱ ነው የተገለጸው።

አሁን ላይ በሰሜን ለንደኑ ክለብ ያለው ውል ሊጠናቀቅ ከሁለት ዓመት ያነሰ ጊዜ የቀረው ሳሊባ በሪያል ማድሪድ በጥብቅ የሚፈለግ ተጫዋች ሆኖ መቆየቱ ይታወቃል።

ሆኖም ዊሊያም ሳሊባ በአርሰናል ቤት በተጫዋችነት ለመቀጠል ፋቃደኛ መሆኑን የ ዘ አትሌቲክ መረጃ ያስረዳል።

አርሰናልም በሚቀጥሉት ቀናት ወሳኝ ተከላካዩ ውሉን ማራዘሙን ይፋ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

እንደ አውሮፓውያኑ በ2019 ከሀገሩ ክለብ ሴንት ኤቲኤን ለአርሰናል የፈረመው ሳሊባ ውሉን የሚያራዝም ከሆነ በዚህ ዓመት ለአርሰናል ኮንትራቱን ያራዘመ አምስተኛው ተጫዋች ይሆናል።

በቅርቡ አጣማሪው ጋብርኤል ማጋሌሽ፣ ኤታን ዋኔሪ፣ ሌዊስ ስኬሊ እና ሊያንድሮ ትሮሳርድ በአርሰናል ለመቆየት ውላቸውን ማደሳቸው ይታወሳል።

ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ