አትሌት ፅጌ ድጉማ እና ወርቅነሽ መሰለ ለግማሽ ፍፃሜ ደረሱ
በቶኪዮ እየተካሄደ በሚገኘው 20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ800 ሜትር ማጣሪያ ውድድር አትሌት ፅጌ ድጉማ እና ወርቅነሽ መሰለ ለግማሽ ፍፃሜ ደርሰዋል።
በማጣሪያው 3ኛው ምድብ ላይ ሆና የተካፈለችው አትሌት ፅጌ ድጉማ ቀዳሚ ሆና በማጠናቀቅ ወደ ቀጣዩ ዙር ተሻግራለች።
በምድብ አምስት የተካፈለችው አትሌት ወርቅነሽ መሰለ በበኩሏ 3ኛ ደረጃን ይዛ በማጠናቀቅ ወደ ግማሽ ፍፃሜው አልፋለች።
በምድብ ሁለት ሆና የተካፈለችው አትሌት ንግስ ጌታቸው ውድድሯን 8ኛ ደረጃን ይዛ በማጠናቀቋ ቀጣዩን ዙር አልተቀላቀለችም።
የሴቶች 800 ሜትር ግማሽ ፍፃሜ ሩጫ ውድድር በነገው ዕለት ከቀኑ 8 ሰዓት ከ45 ደቂቃ ላይ ይካሄዳል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
የባርሴሎና ቀዳሚ ተመራጭ
ጤናማ እና አምራች ዜጋን ለመፍጠር በጤና ስፖርት ቡድኖች የሚሳተፍ ማህበረሰብ መገንባት ወሳኝ መሆኑን የጎፋ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ገለጸ
ማንቸስተር ሲቲ የፊል ፎደን ውል ለማራዘም ስራ መጀመሩ ተገለፀ