የፍቅር፣ የሠላም፣ የአንድነትና መተሳሰብ መገለጫ የሆነውን “ዮ…ማስቃላ” የዘመን መለወጫ በዓል በዞን ደረጃ በድምቀት ለማክበር ዝግጅት መጠናቀቁን የጋሞ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ አሰታወቀ
ከፈደራል ጀምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በበዓሉ ላይ እንደሚታደሙ ተመላክቷል።
ጋሞ ዞን ሶስት ነባር ብሄረሰቦች ያሉበት ሲሆን የጋሞ፣ ዘይሴ እና ጊዲቾ ብሔረሰቦች የዘመን መለዋወጫ እንደየአካባቢው ነባራዊ ሁኔታ በጋራ እንደሚከበር የጋሞ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ አቶ ሞናዬ ሞሶሌ ተናግረዋል።
”የዮ…ማስቃላ” ዘመን መለወጫ በዓል ለሰው ልጆች ብቻም ሳይሆን ለእንስሳት እና ለአእዋፋት ጭምር ነው ተብሎ ይታመናል።
በዓሉን በድምቀት ለማክበር የሚደረገው ዝግጅት አንድ ዓመት ይፈጃል ያሉት አቶ ሞናዬ፤ ለዝግጅቱ አባቶች፣ ወጣቶች እና ልጆች በተለይ ደግሞ የእናቶች ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን አብራርተዋል።
በዚህም በተለያየ ምክንያት የተጣሉ ታርቀው፣ የተራራቁ ዘመድ አዝማድ እና ወዳጆች ተሰባስበውና ያዘኑት ሀዘናቸውን ትተው በዓሉን በጋራ እንዲያከብሩ ማድርግ የጋሞ ‘ማስቃላ’ መግለጫ መሆኑን ኃላፊው ጠቅሰዋል።
የ”ዮ…ማስቃላ” ዘመን መለወጫ በዓል፣ ፍቅር፣ ሠላም፣ አብሮነትና መተሳሰብን የሚያጠናክር በዓል መሆኑን የገለፁት አቶ ሞናዬ፤ ባህሉ ተጠብቆ እንዲቆይ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በተለይም በዓሉ ህብረ ብሄራዊነት የሚዘከርበት በመሆኑ ባህሉ እንዲጎለብት መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል።
በዓሉን ባህላዊ እና ሀይማኖታዊ ዕሴትን በጠበቀ መልኩ ለማክበርና ለማስተዋወቅ ብሎም “ዱቡሻ እና የዲቡሻ ወጋን” በዩኔስኮ ለማስመዝገብ የሚደረገውን ጉዞ ዳር ለማድረስ ከፌደራል ጀምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚታደሙ አቶ ሞናዬ አመላክተዋል።
ዘጋቢ፡ አለሚቱ አረጋ – ከአርባምንጭ ጣቢያችን
የፍቅር፣ የሠላም፣ የአንድነትና መተሳሰብ መገለጫ የሆነውን “ዮ…ማስቃላ” የዘመን መለወጫ በዓል በዞን ደረጃ በድምቀት ለማክበር ዝግጅት መጠናቀቁን የጋሞ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ አሰታወቀ

More Stories
ምግብና ሥርዓተ-ምግብን በማሻሻል የቤተሰብ ብልጽግናን ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ ገለጸ
የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በምርምር የተረጋገጡ አዳዲስና የተሻሻሉ ቴክኖሎጂዎችን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ
የቀይ አፈር ሙሉ ወንጌል ነህምያ የልጆች ልማት ከደቡብ ኦሞ ዞን ሴቶችና ሕፃናት መምሪያ ጋር በመተባበር “የዎና ናና” የህፃናት ልማት ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ በዲመካ ከተማ ተካሂዷል