የህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለመላው የጥቁር ህዝቦች ኩራት ነው – የኮሬ ዞን አስተዳደር
ሀዋሳ፡ መስከረም 06/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) የህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለመላው የጥቁር ህዝቦች ኩራት መሆኑን የኮሬ ዞን አስተዳደር አስታወቀ፡፡
በኮሬ ዞን ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምርቃትን በተመለከተ በፓናል ውይይትና በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት ተከብሯል ።
በዚህ ወቅት ንግግር ያደረጉት የኮሬ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታረቀኝ በቀለ ታላቁ የህዳሴ ግድባችንን የኢትዮጵያውያን ተጋድሎ የታየበትና ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካዊያን ኩራት መሆኑን ገልጸዋል ።
የእንጉርጉሮ ዘመን አብቅቶ የህዳሴ ግድብ ተመርቆ በአይናችን አይተናል ያሉት አስተዳዳሪው፥ በዚህ ብቻ ሳንገታ ኢትዮጵያን ለአለም ሊያሳዩ የሚችሉ ትላልቅ ፕሮጀክቶችን መስራት እንደሚቻል ይህ ማሳያ እንደሆነ ነው የተናገሩት ።
የኮሬ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ሳድሁን በበኩላቸው የህዳሴ ግድብ፣ ኢትዮጵያ ታላቅነቷ በአለም መድረክ የታየበት፣ የአንድነታችን ማረጋገጫ ካርታችን ነው ብለዋል ።
በኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነት በብልጽግና ተምሳሌት የህዳሴ ግድባችንን አጠናቀናል፤ በሌሎች ሀገራዊ ስራዎች በህዳሴ ያሳየነውን አንድነትና ቁርጠኝነት ማስቀጠል ይገባናል ነው ያሉት ።
የውይይቱ ተሳታፊዎችም የህዳሴ ግድባችን የነበሩ ልዩነቶችን ያጠበበ፣ በራሳችን ገንዘብና ላብ የተገነባ የሁላችንም አሻራ ያረፈበት ነው ሲሉ ገልጸዋል ።
እኛም የዚህ ትውልድ አካል በመሆናችን ዕድለኞች ነን የሚሉት ተሳታፊዎቹ በሌሎችም ፕሮጀክቶች አንድነታችንን ማጠናከር አለብን ብለዋል።
የታላቁ ህዳሴ ግድብ መመረቅን አስመልክቶ በተካሄደው የድጋፍ ሰልፍ ላይ መሪ ቃሎችና የተለያዩ መልዕክቶችን በማስተላለፍየዕለቱ ዝግጅት ተጠናቋል።
ዘጋቢ: ለምለም ኦርሳ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
More Stories
ግድባችን የአባይ ዘመን ትውልድ ትክክለኛ ሀሳብ፣ በትክክለኛ ጊዜ የገነባነው ዘመን ተሻጋሪ ቅርሳችን ነው ሲሉ በደቡብ ኦሞ ዞን የበና ፀማይ ወረዳ ነዋሪዎች ገለፁ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተያዘው በጀት ዓመት ከ2 ሺህ 291 ኪሎ ሜትር በላይ የጠጠር መንገድ እና 112 ድልድዮች ይገነባሉ
የዘንድሮው የሀዲያ ብሔር ዘመን መለወጫ “ያሆዴ” በዓል ሲከበር የተቸገሩትን በመደገፍ፣ በመተሳሰብ እና ያለውን ተካፍሎ በመብላት ሊሆን እንደሚገባ ተገለጸ